- Aptis በድርጅትዎ ውስጥ ያሉትን ሠራተኞች የእንግሊዝኛ ችሎታ ውጤታማ እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ መገምገም የሚያስችል ፕሮግራም ነው።Aptis በድርጅትዎ ያሉት ሠራተኞች ስላላቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ አስተማማኝ እና ትክክለኛ የሆነ ውጤት በማሳየት በሠራተኛ ቅጥር፣ በሠራተኛ ሃይል ልማት እና በሥልጠና ረገድ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ማድረግ እንዲችሉ ይረዳዎታል።
- Aptis በሚፈልገው መልክ ሊስተካከል እና በቀላሉ ሊገኝ የሚችል ፕሮግራም በመሆኑ የሠረተኞችዎን ችሎታ በፍጥነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ መገምገም ያስችልዎታል።
- እንዲሁም እርስዎ ከሚፈልጉት ብቃት አንፃር በትክክል መፈተን እና በፍጥነት ውጤት ማግኘት ያስችልዎታል።
ፈተናው የተዘጋጀው እንዴት ነው?
- Aptis የሰዋስው፣ የቃላት እውቀት እና የቋንቋ ችሎታዎች ፈተና (የመናገር፣ የመጻፍ፣ የማንበብ እና የመስማት)። እያንዳንዱ ተፈታኝ የሰዋስው እና የቃላት እውቀት ፈተና ከተፈተነ በኋላ እርስዎ የመረጡትን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ፈተና ይፈተናል።
- ፈተናዎቹ አጠቃላይ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎች በማንሳት ይጀምሩና ይበልጥ ወሰብሰብ ያሉ ሥራዎችን ወደ መሥራት ይሸጋገራሉ። በእያንዳንዱ የፈተና ክፍል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ይገመገምና A1-C ያሉት ደረጃዎች ይሰጣሉ።
የሚፈልጉትን የ APTIS ፈተና መምረጥ የሚችሉት እንዴት ነው?
ሁሉንም የፈተና አይነቶች (የመናገር፣ የመጻፍ፣ የማንበብ እና የመስማት) መምረጥ ይችላሉ አሊያም ደግሞ ለድርጅትዎ ይበልጥ የሚያስፈልገውን ብቻ መምረጥ ይችላሉ።
ለምሳሌ ያህል እንግዳ የሚስተናገድበት ቢሮ ውስጥ ሠራተኛ የመቅጠር ሃላፊነት ያለብዎት የሰው ሃይል ክፍል ሥራ አስኪያጅ ከሆኑ እንግሊዝኛ የመናገር እና የመጻፍ ችሎታ ላይ ማትኮር ሊኖርብዎት ይችላል። ይሁንና የአስተማሪዎችዎትን አጠቃላይ የቋንቋ ችሎታ መገምገም ከፈለጉ በአራቱም መስኮች ማለትም በመናገር፣ በመጻፍ፣ በመስማት እና በማንበብ ረገድ ግምገማ ማካሄድ ይገባዎታል።
እርስዎ በምን መንገድ በ Aptis ቢጠቀሙ በጣም የተሻለ እንደሚሆን ምክር ልንለግስዎት እንችላለን።
ፈተና መፈተን የፈለጉት ሠራተኛ ለመቅጠር ወይም ለሠራተኛ ሃይል ልማት አሊያም ደግሞ ስልጠና ለማካሄድ ቢሆን፣ Aptis እርስዎ ሲጠባበቁት የቆዩ አንድ እርምጃ ወደፊት የሄደ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና ነው።
Aptis ቫሪያንትስ
ፈተናውን ለድርጅትዎት በሚያስፈልገው መልኩ አስተማማኝ የሆነ እና ትክክለኛ ውጤት ማግኘት እንዲያስችል አድርገው ማስተካከል ይችላሉ።
Aptis ጀነራል
Aptis ጀነራል መሰረታዊ የግምገማ ፈተና ነው። ለንግድዎት ወይም ለድርጅትዎት እንደሚያስፈልግ ሆኖ መስተካከል ይችላል፤ ለምሳሌ ያህል ለተለዩ የሥራ መስኮች (ለምሳሌ፦ የንግድ፣ የጉዞ፣ የአስጎብኚ) እና ሙያዎች እንደሚመች ተደርጎ መስተካከል የሚችል ነው።
Aptis ለአስተማሪዎች
Aptis ለአስተማሪዎች የተዘጋጀው በተለይ በማስተማር ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በእርስዎ ተቋም ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት በተሻለ ጥራት እንዲያቀርቡ ታስቦ ነው።
ስለ Aptis ለአስተማሪዎች ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይመልከቱ።