Aptis በመላው ዓለም የሚገኙ ሁሉም አይነት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች እና የቋንቋ ትምህርት ቤቶች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ደረጃ መለኪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ብሪቲሽ ካውንስል ያዘጋጀው ፕሮግራም ነው።

Aptisን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታን ለማሳደግ እና ለስልጠና ባወጡት ፕሮግራም ውስጥ በማካተት ሊጠቀሙበት ይችላሉ። የሚያሰለጥኑት በአካል ተገኝተውም ይሁን በልዩ ልዩ መንገዶች አሊያም ደግሞ ኢንተርኔት ላይ በሚገኝ ማስተማሪያ፣ Aptisን ለቅድመ እና ለድህረ ግምገማ መጠቀም ይችላሉ። በዚህ መንገድ ከስልጠናው ‘በፊት’ እና ‘በኋላ’ በያዙት የግምገማ መረጃ ተጠቅመው የምን ያህል ተማሪዎች ችሎታ እንደተሻሻለ ማወቅ ይችላሉ።

Aptis ከ ኮመን ዩሮፒያን ፍሬምወርክ ኦፍ ሬፈረንስ ፎር ላንጉዌጅስ ጋር እኩል የሆነ ዓለም አቀፍ መስፈርት በመሆኑ የሠራተኞችዎትን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ በአስተማማኝ ሁኔታ መገምገም ያስችልዎታል።

በዚህ ክፍል ውስጥ

የመንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ወይም መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ናችሁ?

Aptis በዓለም አቅፍ ደረጃ እንደ መሥፈርት ተደርጎ የሚወሰድ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና ሲሆን በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ለመስጠት እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከል ከመሆኑም ሌላ በአሁኑ ጊዜ ግለሰቡ ያለው የችሎታ ደረጃ ምንም ሆነ ምን ለማንኛውም ተፈታኝ ተስማሚ ነው።