Aptis ምንድን ነው?
በዓለም ዙሪያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና በመስጠት ረገድ የ70 ዓመት ልምድ አለን። ባለሙያዎቻችን በቅርብ በተገኙ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ መገምገሚያዎች ላይ ተመሥርተው የAptis ፈተና አዘጋጅተዋል።
Aptis በሁሉም የቋንቋ ክህሎቶች ማለትም በመናገር፣ በመጻፍ፣ በማንበብ እና በመስማት የእንግሊዝኛ ችሎታዎን መመዘን ይችላል። እንዲሁም የሰዋስውና የቃላት እውቀት ፈተናን ያካትታል። የትኞቹን የክህሎት ፈተናዎች እንደሚፈተኑ የሚወስነው ፈተናውን እንዲወስዱ ጥያቄ ያቀረበው ድርጅት ነው (ለምሳሌ፣ አሠሪ ወይም ሥልጠና ሰጪ)።
የAptis ፈተና መፈተን የምችለው እንዴት ነው?
የAptis ፈተናን በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ የሚያቀርብልዎት የእርስዎ አሠሪ፣ ዩኒቨርሲቲ ወይም ትምህርት ቤት ይሆናል። በቀጥታ እኛ ዘንድ መጥተው መመዝገብ አይችሉም።
ያገኘሁት ውጤት ምን ያሳያል?
የሚሰጥዎት ውጤት በኮመን ዩሮፒያን ፍሬምወርክ ኦፍ ሬፈረንስ ፎር ላንጉዌጅስ (CEFR) ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ያገኟቸው ውጤቶች ለእያንዳንዱ የክህሎት ፈተና ያገኙትን የCEFR (A1-C) ደረጃ ያሳያል። የአራቱንም የክህሎት ዘርፎች ፈተናዎች ከወሰዱ አጠቃላዩን የ CEFR ደረጃ የሚያንጸባርቅ ውጤት ያገኛሉ። ካገኙት የ CEFR ደረጃ በተጓዳኝ በእያንዳንዱ የክህሎት ፈተና ያለዎትን ችሎታ የሚያሳይ ውጤት በደረጃ (0-50) ይሰጥዎታል።
የፈተና ሪፖርት ናሙናውን ይመልከቱ።