የመናገር ፈተና 4 ክፍሎች ያሉት ሲሆን 12 ደቂቃዎችን ገደማ ይፈጃል።

የሰጧቸው መልሶች ተቀድተው ይቀመጣሉ፤ በመቀጠልም የብሪቲሽ ካውንስል ፈታኝ ውጤት ይሰጥዎታል። ጥቂት ጠቃሚ ሃሳቦች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦  

  • ጥያቄውን በሚገባ ይገንዘቡ፤ በትክክለኛው መንገድ የተሟላ መልስ ይስጡ።
  • ዘርዘር ያለ ወይም ሰፊ መልስ ለመስጠት ይሞክሩ።
  • በድምፅ ማጉያው በአግባቡ እየተጠቀሙ መሆንዎን እርግጠኛ ይሁኑ፤ ጊዜዎንም በሚገባ ይቆጣጠሩ።
  • የፈተናው ቀን ከመድረሱ በፊት የቻሉትን ያህል የንግግር ልምምድ ያድርጉ፤ እሳሳት ይሆናል ብለው ብዙም አይጨነቁ፤ ከዚህ ይልቅ መልእክትዎትን በአግባቡ ማስተላለፍዎት ላይ ያተኩሩ።
  • እየተናገሩ ሳሉ ራስዎን ይቅዱ፦ የቃላት እውቀትዎንና የቃላት አጠራርዎችን ለማሻሻል ይሞክሩ፤ ብዙም ቆም ላለማለት ይጣሩ።

ውጫዊ ማያዣዣዎች