የድርጅትዎ ሠራተኞች ለሥራው የሚያስፈልግ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እንዳላቸው እንዴት ማወቅ ይችላሉ?

Aptis የድርጅትዎ ሠራተኞች ወይም ሊቀጥሯቸው ያሰቧቸው ሰዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ደረጃ ምን እንደሆነ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኙ ያስችልዎታል።

ይህም ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነጥቦች ይበልጥ ቀላል እንዲሆንልዎት ያደርጋል፦

  • ትክክለኛዎቹን ሰዎች ለመቅጠርና የሥራ እድገት እንዲያደርጉ ለመርዳት፣
  • ካወጡት ወጪ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ ስልጠናው ይበልጥ አስፈላጊ በሆኑ መስኮች ላይ ያተኮረ እንዲሆን፣
  • እርስዎ ጋር ተቀጥረው የሚሠሩ ሰዎች ያላቸውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እንዲሁም ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን ለይተው ማወቅ እንዲችሉ ይረዳዎታል።

APTISን ቢመርጡ ምን ጥቅም ያገኛሉ?

  • Aptis እርስዎ በመረጡት ቦታና ጊዜ አመቺ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ፕሮግራም ለማውጣት ምንም አይቸገሩም።
  • የተለያዩ የቋንቋ ችሎታዎችን ለመገምገም እንዲያስችል ተደርጎ የተቀመረ ነው - የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የመስማት እንዲሁም የሰዋስውና የቃላት እውቀት ችሎታ ላይ ያነጣጥራል።
  • ለድርጅትዎ የሚስማማውን የሥልጠና ዓይነት ብቻ መምረጥ ይችላሉ።
  • Aptis ታብሌቶችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ እስክርቢቶዎችንና ወረቀቶችን ጨምሮ በብዙ የመረጃ ማስቀመጫዎች ላይ ለፈተናው ሊቀመጡ ይችላሉ፤ ይህም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለፈተናው ለማስቀመጥ ምቹ ያደርገዋል።
  • የተለያዩ የቋንቋ ችሎታ ደረጃዎችን ማለትም ከ A1 እስከ C ያሉትን ደረጃዎች መመዘን ይችላሉ፤ ይህም በተመሳሳይ ዓይነት ፈተናና በተመሳሳይ ጊዜ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑትንም ሆነ በጣም ደካማ የሆኑትን ሰዎች በትክክል ለመመዘን ያስችልዎታል።

በAPTIS የሚጠቀሙት ምን ዓይነት የንግድ ተቋማት ናቸው?

አዴኮ ፖላንድ፣ የአዴኮ ግሎባል ቅርንጫፍ ሲሆን ለሰው ኃይል ጉዳዮች መፍትሔ በመስጠት ረገድ ግንባር ቀደም የሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው።

አዴኮ ደንበኞች ሲመጡ ተቀብለው የሚያስተናግዱ ሠራተኞችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ደረጃቸውን ለመፈተን በAptis ተጠቅሟል፤ ደንበኞችን የሚያስተናግዱ ተቀጣሪዎች ተቀዳሚ ሥራ ከEMEA የሚመጡ የውጭ ደንበኞችን የሚፈልጓቸውን የአገልግሎት ዓይነቶች በ11 ቋንቋዎች መመዝገብ ነው።

 ለገንዘብ እና ለኪራይ ኢንዱስትሪ የኮምፒውተር መረጃ አገልግሎት የሚሰጥ ዓለም አቀፍ ድርጅት

NetSol የተባለው ድርጅት የተለያዩ የሥራ መደቦች የሚጠይቁትን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ መሥፈርት ለማውጣትና ሥራው የሚጠይቀው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እንዲኖራቸው ሠራተኞችን በመመዘን ምን ዓይነት ሥልጠና እንደሚያስፈልጋቸው ለመገምገም በAptis ተጠቅሟል። ከዚህ በተጨማሪ ሠራተኞች አወዳድሮ የመቅጠር አጠቃላይ ሂደቱ ይበልጥ የተቀላጠፈ እንዲሆን Aptis ጥቅም ላይ ውሏል።

ውጫዊ ማያዣዣዎች