የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታን በትክክል መመዘን የሚቻለው እንዴት ነው?

Aptis ዓለም አቀፍ የእንግሊዝኛ ፈተና መሥፈርት ሲሆን በሚከተሉት መንገዶች ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፦

  • የእንግሊዝኛ ቋንቋ የማጎልበቻ ፕሮግራም ክፍል አድርጋችሁ፣
  • መምህራናችሁ ወይም ተማሪዎቻችሁ የሚያስፈልጋቸውን ሥልጠና ለይታችሁ ለማወቅ መገምገሚያ ዘዴ አድርጋችሁ፣ <Link to teacher and students pages>
  • በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ፣ አጋማሽ እና ማብቂያ ላይ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የማስተማሪያ ፕሮግራማችሁን ውጤታማነት ለመመዘን፣
  • የተፈታኞችን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ለይቶ ለማወቅ።

ያሉት ጥቅሞች፦

  • Aptis በግለሰብ ደረጃ ለአመልካቾች ተስማሚ የሆኑ ሁኔታዎችን ይጠቀማል፣
  • የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የመስማት ችሎታዎችን መገምገም፤ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ብቻ ወይም የተወሰኑትን አጣምሮ ማስኬድ ይቻላል፣
  • የመናገርና የመጻፍ ችሎታ የሚገመገመው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ቡድን ሲሆን ይህም ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ለመጠበቅ ያስችላል፣
  • Aptis በተለያየ መልክ፣ በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ሊሰጥ ይችላል፤ በውጤቱም ፈጣን መሻሻል ይገኝበታል።

Aptis እንደ ሁኔታው የሚስተካከል፣ ሚዛናዊነት እና ተቀባይነት ያለው ፈተና ነው፤ በመሆኑምተማሪዎቻችሁን ወይምአስተማሪዎቻችሁን በአስተማማኝ ሁኔታ እንድትመዝኑ የሚያስችላችሁ ከመሆኑም ሌላ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን በተመለከተ ትክክለኛና አስተማማኝ ውጤት ይሰጣችኋል። <Link to teacher and students pages>

ውጤቶች የሚታዩት ዓለም አቀፋዊ መሥፈርት በሆነው ኮመን ዩሮፒያን ፍሬምወርክ ኦፍ ሬፈረንስ ፎር ላንጉዌጅስ ነው፤ ይህ ደግሞ ማሻሻል የሚያስፈልግበትን አቅጣጫ በቀላሉ ለማወቅ በማስቻል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኮርሶች ወይም ሥልጠናዎች በሚፈለገው መልክ እንዲዘጋጁ መንገድ ይከፍታል።

ይህም በትምህርት ቤታችሁ፣ በኮሌጃችሁ ወይም በዩኒቨርሲቲያችሁ የእድገት ፕሮግራም ውስጥ የቅድመ እና የድህረ ግምገማ ዝግጅት ክፍል ተደርጎ ሊካተት ይችላል። ትምህርቱ የሚሰጠው በግንባር በመቅረብ ወይም በኢሜይል በመማር አሊያም በሁለቱም መንገድ በመሠልጠን/በመማር ሊሆን ይችላል።

APTIS ለተቋማችሁ ይህን ለማከናወን በዓይነቱ ልዩ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛል የምንለው ለምንድን ነው?

  • ፈትናችሁ ማየት የምትፈልጉትን ማንኛውም ችሎታ (የመጻፍ፣ የማንበብ፣ የመናገርና የመስማት ችሎታ) መቀላቀልና ማጣመር ትችላላችሁ።
  • የAptis ፈተና በራሳችሁ ስም ለማዘጋጀት የእኛ አጋር መሆን ትችላላችሁ።
  • Aptis የፈተናዎች ይዘት የሚጠናው በብሪቲሽ ካውንስል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ነው።
  • ፈተናው ለአስተማሪዎቻችሁና ለተማሪዎቻችሁ የሚስማማ እንዲሆን ይዘቱን እንደ አስፈላጊነቱ አስተካክለን ማቅረብ እንችላለን።
  • ችሎታችሁን ለማየት በወሰዳችሁት በእያንዳንዱ ፈተና በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ ያገኛችኋቸውን ውጤቶች በዝርዝር የያዘ ሪፖርት ማግኘት ትችላላችሁ

በAPTIS የሚጠቀሙት ምን ዓይነት ተቋሞች ናቸው?

በAptis ከሚጠቀሙ ተቋሞች መካከል የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቋንቋ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍና የግል ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል

External links

Aptis ኬዝ ስተዲ፡- ፑንጃብ ኤጁኬሽን

በዚህ ክፍል ውስጥ