የቋንቋ ችሎታን የሚፈትኑበትን መንገድ እንዲያሻሽሉ ልንረዳዎት እንችላለን።

በዓለም ዙሪያ ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ እንግሊዝኛ የሚማሩ መሆናቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታን የመገምገሙን አስፈላጊነት የማይታለፍ ጉዳይ አድርጎታል። ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ወላጆች፣ ተማሪዎቻቸው እና ልጆቻቸው ወደፊት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው ትምህርት መማር፣ መሻሻል ማድረግ እና ሥራ መሥራት ቢመርጡ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባሉ። ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በተለይ ለትምህርት ቤቶች ታስቦ ሲሆን በወቅቱ ጥቅም ላይ እየዋለ ባለው አሠራር ሙሉ በሙሉ ሊካተት እና በአካባቢው ባሉ አካላት ቁጥጥር ሊደረግበት የሚችል ነው።

ፕሮግራሙ ምንድን ነው? 

 • Aptis ለወጣቶች፣ በብሪቲሽ ካውንስል የተዘጋጀ አዲስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ መገምገሚያ ፕሮግራም ነው፤ ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በተለይ ለወጣቶች ታስቦ ሲሆን በታወቁ ርዕሰ ጉዳዮች እና ሁኔታዎች በመጠቀም ችሎታቸውን መገምገም ያስችላል።
 • ከ 13-17 ዓመት እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀው Aptis ለወጣቶች፣ በተወሰኑ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩ እና ውጤትዎን በፍጥነት ማግኘት እንዲችሉ የሚረዳ ነው።
 • ፈተናው እንዳይከብድ ሲባል ጥያቄዎቹ የተመሰረቱት ወጣቶች በሚያደርጓቸው የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች ላይ ነው፤ ከእነዚህም መካከል ማኅበራዊ ድረገፆች፣ የቤት ሥራ፣ የትምህርት ቤት ዝግጅቶች እና ስፖርቶች ይገኙበታል። ይህ ዘመናዊ መፈተኛ ዘዴ ተፈታኞች የእንግሊዝኛ ቋንቋ እውቀታቸውን እና ችሎታቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማሳየት ያስችላቸዋል።
 • Aptis ለወጣቶች፣ የተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ደረጃ በጊዜ ሂደት ውጤታማ እና ትክክለኛ በሆነ መልኩ መለካት የሚያስችል በወቅቱ ካለው የማስተማሪያ ዘዴ ጋር ተቀላቅሎ ሊሠራበት የሚችል ፕሮግራም ነው።

ማን ሊጠቀምበት ይችላል?

 • መለስተኛ እና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
 • በመላው ዓለም የሚገኙ የትምህርት ሚኒስቴሮች
 • የቋንቋ ትምህርት ቤቶች
 • በግል የሚያስተምሩ አስተማሪዎች
 • በሁለት ቋንቋ የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች

ምን ሊያከናውን ይችላል?

 • እጅግ ዘመናዊ የሆነ ብቃት ያላቸውን ተማሪዎችን ለማፍራት
 • የምሥክር ወረቀት የሚያስገኝ ፈተና ለመፈተን ዝግጁ መሆንን ለመገምገም
 • በውጪ እና በአገር ውስጥ ባሉ ፕሮግራሞች ለመማር ዝግጁ መሆንን ለመገምገም
 • የአንድን የማስተማር ዘዴ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ለመለየት እና ለማሳወቅ እንዲሁም ለተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ
 • የትምህርት ፕሮግራሞችን ለመገምገም
 • ለረጅም ጊዜያት የሚማሩ ተማሪዎች እያሳዩ ያሉትን መሻሻል ለመፈተሽ።

ሪፖርት የምንሰጥበትም መንገድ እንደ አመቺነቱ ሊስተካከል ይችላል፤ የፈተና ውጤቶች በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ ተዘጋጅተው ይቀርባሉ።

ለእያንዳንዱ የክህሎት ፈተና በደረጃ ውጤት (0-50) የሚሰጥ ሲሆን በዚህ አማካኝነት ዕጩዎችን በግለሰብ ደረጃ ለማነጻጸር ብቻ ሳይሆን ተፈታኞቹ ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱ ከሆነ ያሳዩትን መሻሻል ለመለካት ሊረዳም ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ በ Common European Framework of Reference for Languages (CEFR) መሰረት ለሁሉም የክህሎት ዘርፎች የደረጃ ውጤት (A1-C) እንሰጣለን። በአራቱ የክህሎት ዘርፎች ሁሉም ፈተናዎች ከተወሰዱ አጠቃላዩን የCEFR ደረጃ የሚያንጸባርቅ ውጤት ማግኘት ይቻላል።

ይህን ደግሞ ይመልከቱ