በ Aptis በመጠቀም በድርጅታችሁ ውስጥ የሚነገረውን እንግሊዝኛ ቋንቋ መገምገምና መመዘን ቀላል ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ መሥፈርት ተደርጎ የሚወሰደው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ለመስጠት እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከል ከመሆኑም ሌላ በአሁኑ ሰዓት ግለሰቡ ያለው የችሎታ ደረጃ ምንም ሆነ ምን ለማንኛውም ተፈታኝ ተስማሚ ነው።
- የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ወይም መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደመሆናችሁ መጠን በአሁኑ ሰዓት የምትሰጧቸውን የእንግሊዝኛ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች በAptis በመገምገም ማጠናከር ትችላላችሁ። ፈተናውን በማንኛውም ሥልጠና መጀመሪያ፣ መካከለኛ እና መጨረሻ ደረጃ ላይ በመፈተን የተፈታኞችን መሻሻል በትክክል መገምገም ይቻላል።
- ለተለያዩ ሠራተኞች የሚያስፈልገውን ሥልጠና ለይታችሁ ለማወቅ Aptisን እንደመመዘኛ አድርጋችሁ መጠቀምም ትችላላችሁ።
- Aptisን ለእናንተ ፍላጎት እንዲስማማ አድርገን ማዘጋጀት እንችላለን።
APTISን ቢመርጡ ምን ጥቅም ያገኛሉ?
- Aptis እርስዎ በመረጡት ቦታና ጊዜ አመቺ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ፕሮግራም ለማውጣት ምንም አይቸገሩም።
- የተለያዩ የቋንቋ ችሎታዎችን ለመገምገም እንዲያስችል ተደርጎ የተቀመረ ነው - የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የመስማት እንዲሁም የሰዋስውና የቃላት እውቀት ችሎታ ላይ ያነጣጥራል።
- ለድርጅትዎ የሚስማማውን የሥልጠና ዓይነት ብቻ መምረጥ ይችላሉ።
- Aptis ታብሌቶችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ እስክርቢቶዎችንና ወረቀቶችን ጨምሮ በብዙ የመረጃ ማስቀመጫዎች ላይ ሊቀመጥ ይችላል፤ ይህም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለማስቀመጥ ምቹ ያደርገዋል።
- የተለያዩ የቋንቋ ችሎታ ደረጃዎችን ማለትም ከ A1 እስከ C ያሉትን ደረጃዎች መመዘን ይችላሉ፤ ይህም በተመሳሳይ ዓይነት ፈተናና በተመሳሳይ ጊዜ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑትንም ሆነ በጣም ደካማ የሆኑትን ሰዎች በትክክል ለመመዘን ያስችልዎታል።