Aptis ለአስተማሪዎች የተባለው ፕሮግራም፣ የመደበኛው Aptis አንዱ ገጽታ ነው። በመላው ዓለም የሚገኙ የትምህርት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና የትምህርት ተቋሟት፣ የአስተማሪዎቻቸውን ወይም የመምህራን ሥልጠና ፕሮግራሞችን በመከታተል ላይ ያሉ ተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ለመፈተን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ፕሮግራሙ በተለይ ለትምህርት ዘርፍ ተብሎ የተዘጋጀ ነው፤ በአሁኑ ወቅት እየተሠራበት ካለው አሠራር ጋር ሙሉ በሙሉ ማዋሃድ የሚቻል ከመሆኑም ሌላ እዚያው ያሉ ሰዎች ሊቆጣጠሩት ይችላሉ፤ ይህም የአስተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ በጊዜ ሂደት ለመከታተል ከማስቻሉም በተጨማሪ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ስኬት በትክክል ለመለካት ያስችላል።
የ Aptis ለአስተማሪዎች እና የመደበኛው Aptis አወቃቀር እና ርዝመት ተመሳሳይ ነው፤ ይሁንና ፈተናው የሚያተኩረው በተለይ በአስተማሪዎች ላይ ሲሆን ጥያቄዎቹ የሚያነጣጥሩት ደግሞ አስተማሪዎች በየእለቱ በሚያጋጥማቸው ጭብጥ እና ሁኔታ ላይ ነው። በዚህም ምክንያት፣ ተፈታኞች ጥያቄዎቹን የሚያውቋቸው ከመሆኑም በላይ ትኩረት የሚያደርጉት በጥያቄው አውድ ላይ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ በቋንቋው ላይ ይሆናል።
APTIS ለአስተማሪዎች የተባለውን ፕሮግራም ለፈተና መጠቀም ይቻላል፦
- በአለም ዙሪያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪዎች
- በአለም ዙሪያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የሌሎች የትምህርት አይነቶች አስተማሪዎች
- በክፍያ የሚሰጡትን ጨምሮ ሰፊ በሆኑ የቋንቋ ፕሮግራሞች ውስጥ የሚሠሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪዎች
- በመምህራን ማሰልጠኛ ወይም በዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሞች ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች
- ከትምህርት ጋር ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን የሚሠሩ ሌሎች ባለሙያዎች።