Federal police officer
Ethiopian Peacekeeping English Project ©

Credit Genaye Eshetu

ብሪቲሽ ካውንስል በ40 አገሮች የሚገኙ ሰላም አስከባሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን እንዲያሻሻሉ ድጋፍ ማድረግ የጀመረው እ. ኤ. አ. ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ እንደሆነ ማስረጃዎች ያሳያሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከአገር መከላከያ ሚኒስቴርና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በጋራ የምንሠራባቸው ማዕከሎች ያቋቋምን ሲሆን በእነዚህ ቦታዎች ወደፊት ሰላም በማስከበር ሥራ ላይ የሚሰማሩ ኢትዮጵያውያንን እናሠለጥናለን፤ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እንዲኖራቸው ያስችላል።

 በመላው አገሪቱ ለሚገኙ አስራ ሁለት የቋንቋ ማዕከሎች የተለያዩ የትምህርት መሣሪያዎችን እናቀርባለን፤ እንዲሁም ለ60 ሲቪል የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪዎች፣ ለኢፌዴሪ አገር መከላከያ እና ለፌዴራል ፖሊስ ባለሥልጣናት ጥልቀት ያለው የቋንቋ እና የማስተማር ዘዴዎች ላይ ሥልጠና ሰጥተናል። ከዚህም በላይ እነዚህን ትምህርት ቤቶች አዘውትረን በመጎብኘት መምህራኑ ሲያስተምሩ ካየን በኋላ ምክር እንለግሳቸዋለን።

ስልጠናውን መስጠት ከጀመርንበት እ.ኤ.አ. ከ2008 ጀምሮ ትምህርቱን ከወሰዱት የሠራዊቱ አባላት መካከል 80% የሚሆኑት ሰላም ለማስከበር መዝመታቸው እንዲሁም አብረዋቸው የዘመቱ የሌሎች አገራት ዜጎች የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት የሚናገሩት እንግሊዝኛ እየተሻሻለ መምጣቱን መናገራቸው ምን ያህል እንደተሳካልን የሚያሳይ ማስረጃ ነው።

 በተጨማሪም በሶማሌላንድ እና በጅቡቲ የሰላም አስከባሪዎች ማዕከሎች አሉን። በሶማሌ ላንድ ውስጥ በሃርጌሳ እና በበርበራ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ማዕከሎች ያሉን ሲሆን በጅቡቲ ደግሞ አንድ ማዕከል አለን። በኢትዮጵያ የሚገኘው ቡድናችን ከላይ በተጠቀሱት ሁለት አገሮች የሚገኙትን ማዕከሎች የሚያስተባብር ሲሆን ለአስተማሪዎቹ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ያደርግላቸዋል።

ውጫዊ ማያዣዣዎች