Africa Knowledge Transfer Partnerships ©

Credit Genaye Eshetu

ፎቶ፦ ገናዬ እሸቱ

ባለንበት የውድድር አለም፣ የግል ተቋማት ምርታማነታቸውን ለማሳደግ አዳዲስ መንገዶችን የመቀየሳቸው አስፈላጊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

አፍሪካ ኖውሌጅ ትራንስፈር ፓርትነርሺፕ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል ድርጅቶች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርምር፣ ሳይንሳዊ እውቀት እና የአዳዲስ ግኝቶች ችሎታ እንዲስፋፋ ለማድረግ አጋርነት እንዲፈጥሩ ታስቦ የተዘጋጀ የሙከራ ፕሮጀክት ነው።

 ይህ ፕሮግራም፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የግል ድርጅቶች በትብብር በሚያዘጋጇቸው ፕሮጀክቶች አማካኝነት ከተቋማቱ የሚገኘውን ሳይንሳዊ እውቀት፣ ቴክኖሎጂ እና ችሎታ በመጠቀም ድርጅቶች ውጤታማነታቸውን እና ተወዳዳሪነታቸውን ማሻሻል እንዲችሉ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ስለ አፍሪካ ኖውሌጅ ትራንስፈር ፓርትነርሺፕ የበለጠ ለመረዳት እባክዎ መጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይፃፉልን።