ለርን ኢንግሊሽ ፓዝዌይስ አንድ ሰው ያለ ማንም እርዳታ ሊማር የሚችልበት በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኮርስ ነው፤ ይህ ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ ኮርስ የብሪቲሽ ካውንስልን በተግባር የተረጋገጠ የኢንተርኔት መማሪያ ጥበቦችን የያዘ ሲሆን፣ በተፈለገው ጊዜ ሠራተኞችዎ ማግኘት እንዲችሉ የተዘጋጀ ነው። እጅግ በርካታ ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ለማሠልጠን የሚያስችል ወጪ ቆጣቢና ምቹ የሆነ ዘዴ ነው። ይህ ኮርስ አንድ ሰው የደረሰበትን ደረጃ በጥሩ ሁኔታ መከታተል የሚቻልበትና የሌሎች እገዛ እምብዛም ሳያስፈልግ በራስ መማር የሚያስችል ነው። በተጨማሪም በግንባር በመገኘት ለሚወሰደው ሥልጠና የሚረዳና ሠራተኞችዎ እንግሊዝኛ መለማመድ የሚችሉበት ተጨማሪ ምቹ ሁኔታ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። በአሁኑ ጊዜ በ15 አገሮች ውስጥ 82,000 ለሚያህሉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች ኮርሱን በመስጠት ላይ እንገኛለን።
ኮርሱ ምን ነገሮችን ያካትታል?
ለርን ኢንግሊሽ ፓዝዌይስ አዋቂ ለሆኑ የእንግሊዝኛ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን በአውሮፓ የጋራ መዋቅር አራት ደረጃዎች (ከA1 እስከ B2) ዙሪያ የተዋቀረ ነው። ለርን ኢንግሊሽ ፓዝ ዌይስ አንድ ሰው የሌሎች እገዛ ሳያስፈልገው በራሱ የሚማራቸውን ስምንት ኮርሶች ይዟል፤ እያንዳንዱ ኮርስ ከ30 እስከ 40 ሰዓት ይፈጃል። ኮርሶቹ በአጠቃላይ 320 ሰዓታት ይወስዳሉ፤ ዓላማው በኢንተርኔት በሚሰጡ አሳታፊ የሆኑ ልዩ ልዩ ትምህርቶች አማካኝነት የተማሪዎቹን የቋንቋ ችሎታ ማሳደግ ነው። ኮርሶቹ በግል እንዲጠኑ ተደርገው የተዘጋጁ በመሆኑ ተማሪው የሌሎች ድጋፍ በትንሹ ቢደረግለት ሊበቃው አሊያም ደግሞ ምንም ዓይነት ድጋፍ ላያስፈልገው ይችላል።
እያንዳንዱ ኮርስ በተለያዩ ጭብጦች (ለምሳሌ፣ ቤተሰብ፣ ጉዞ፣ ሥራ እና ባሕል) ላይ የሚያተኩሩ ስድስት ክፍሎችን ያቀፈ ነው፤ ኮርሱን በድምፅ ቅጂዎች፣ በጽሑፍ፣ በምስሎች እና በቪዲዮ መከታተል ይቻላል። እያንዳንዱ ክፍል፣ በውስጣቸው ከአምስት እስከ አሥር የሚያህሉ መልመጃዎች የያዙ አምስት ንዑስ ክፍሎች አሉት። ከተለመዱት የመልመጃ ዓይነቶች መካከል አጫጭር ጥያቄዎች፣ ባዶ ቦታ መሙላት፣ ማገናኘት፣ ማዛመድ፣ በቡድን ማስቀመጥ፣ ወዘተ የሚሉት ይገኙበታል። ንዑስ ክፍሎቹ በማጠቃለያና አጠር ባለ ፈተና ይደመደማሉ።
ኮርሱን ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
ተማሪዎች ለየራሳቸው ኮርሶቹን ማግኘት የሚችሉበት አድራሻ ይሰጣቸዋል። ይህም ማለት በኮምፒውተር ፕሮግራሙ ውጤት መመዝገቢያ ላይ ወዲያውኑ የሚመዘገበውን፣ እያደረጉ ያሉትን መሻሻልና ውጤታቸውን የሚያሳየውን መረጃ መከታተል ይችላሉ ማለት ነው። በየሳምንቱ ተማሪው ከኮርሱ ጋር በተያያዘ ያደረገው የመጨረሻ መሻሻል በቀጥታ ወደ የሰው ሃይል ክፍል ኢሜይል ይደረጋል ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ኮርሱን በተመለከተ ያደረጉትን እድገት ወቅታዊ መረጃ ለእርስዎ እንሰጥዎታለን።
በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ለርን ኢንግሊሽ ፓዝዌይስ የተባለው ኮርስ የሚሰጠው ለድርጅቶች፣ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ለትምህርት ተቋማት ብቻ ነው። በኢንተርኔት የሚሰጡ ኮርሶችን በግለሰብ ደረጃ መማር የሚፈልጉ ደንበኛ ከሆኑ በቅርቡ የሚጀመሩትን በኢንተርኔት በነፃ የሚሰጡ ኮርሶችን እዚህ ላይ መከታተል ለምን አይጀምሩም?
ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምችለው የት ነው?
ስለሚወስዱት ሥልጠና ለመነጋገር ወይም ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ መጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን።