ለርን ኢንግሊሽ ሰሌክት አንድ ሰው ያለ ማንም እርዳታ ሊማርበት የሚችል በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ ለሥራ ቦታ እንዲጠቅም ታስቦ የተዘጋጀ አዲስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኮርስ ነው፤ ይህ የኢንተርኔት ኮርስ የብሪቲሽ ካውንስልን በተግባር የተረጋገጡ የኢንተርኔት መማሪያ ጥበቦችን የያዘ ሲሆን፣ በተፈለገው ጊዜ ሠራተኞችዎ ማግኘት እንዲችሉ የተዘጋጀ ነው። እጅግ በርካታ ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ለማሠልጠን የሚያስችል ወጪ ቆጣቢና ምቹ የሆነ ዘዴ ነው። ይህ ኮርስ አንድ ሰው የደረሰበትን ደረጃ በጥሩ ሁኔታ መከታተል የሚቻልበትና የሌሎች እገዛ እምብዛም ሳያስፈልግበራስመማርየሚያስችልነው።
ኮርሱ ምን ነገሮችን ያካትታል?
ለርን ኢንግሊሽ ሰሌክት አዋቂ ለሆኑ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን በአውሮፓ የጋራ መዋቅር አራት ደረጃዎች (ከA0 እስከ B1) ዙሪያ የተዋቀረ ነው። ኮርሱ ወጣት ሠራተኞች ለሥራቸው ያላቸው አመለካከት እንዲሻሻል የሚረዳ ሲሆን እያንዳንዱ ደረጃ 40 ምእራፎች ያሏቸው 8 ክፍሎችን ይዟል (አንዱ ክፍል 5 ምእራፎችንና የዚያን ክፍል የመጨረሻ ፈተና ይይዛል።) እያንዳንዱን ክፍል ለማጠናቀቅ ከ45 – 55 ሰዓታት ይፈጃል።
ኮርሱ በምስልና በድምፅ የሚቀርቡ የተለያዩ የቃላት አጠራሮችን እና አሳታፊ የሆኑ ልምምዶችን ይዟል። የኮርሱ መማሪያዎች ሥራ ቦታ ላይ በሚያጋጥሙ ሶስት የተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ያተኩራሉ፦
- ሥራ መግባት፦ሥራ ለመቀጠር ማመልከት፣ ለቃለ መጠይቅ መዘጋጀት
- በሥራ ቦታ፦ በሥራ ቦታ፣ በስብሰባዎች እና ንግግር በሚቀርብበት ጊዜ ተሳታፊ መሆን (ዘና በሚሉበት እና ከሥራ ቦታ ውጪ ከሰዎች ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ጭምር)
- ሰዎች ፊት መቅረብ፦ በመሥሪያ ቤቱ የሚገኙትን ምርቶችንና አገልግሎቶች ማስተዋወቅ፣ ከተገልጋዮች እና ከደንበኞች ጋር ተባብሮ መሥራት።
ኮርሱን ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
ተማሪዎች ለየራሳቸው ኮርሶቹን ማግኘት የሚችሉበት አድራሻ ይሰጣቸዋል። ይህም ማለት በኮምፒውተር ፕሮግራሙ ውጤት መመዝገቢያ ላይ ወዲያውኑ የሚመዘገበውን፣ እያደረጉ ያሉትን መሻሻልና ውጤታቸውን የሚያሳየውን መረጃ መከታተል ይችላሉ ማለት ነው። በየሳምንቱ ተማሪው ከኮርሱ ጋር በተያያዘ ያደረገው የመጨረሻ መሻሻል በቀጥታ ወደ የሰው ሃይል ክፍል ኢሜይል ይደረጋል ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ኮርሱን በተመለከተ ያደረጉትን እድገት ወቅታዊ መረጃ ለእርስዎ እንሰጥዎታለን።
በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ለርን ኢንግሊሽ ሰሌክት የተባለው ኮርስ የሚሰጠው ለድርጅቶች፣ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ለትምህርት ተቋማት ብቻ ነው። በኢንተርኔት የሚሰጡ ኮርሶችን በግለሰብ ደረጃ መማር የሚፈልጉ ደንበኛ ከሆኑ በቅርቡ የሚጀመሩትን በኢንተርኔት በነፃ የሚሰጡ ኮርሶችን እዚህ ላይ መከታተል ይችላሉ።
ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምችለው የት ነው?
ስለሚወስዱት ሥልጠና ለመነጋገር ወይም ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ መጥተው ያነጋግሩን ወይም በአድራሻችን ይጻፉልን።