Cambridge exam student
©

Credit Ala Kheir

በዚህ ክፍል ውስጥ፣ በመጻፍና በመናገር ፈተናዎች ቀን ምን ማድረግ እንዳለብዎት የሚገልፁ መረጃዎችንና ምክሮችንያገኛሉ።

በመጻፍ ፈተና ወቅት ምን ማድረግ ይገባል?

ፈተናው ከመጀመሩ በፊት

 • እስክሪብቶ፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ ፓስፖርትዎን/የቀበሌ መታወቂያዎትን እና ፕሮግራምዎትን ይዘው ይምጡ
 • ፈተናው ከሚጀምርበት ሰአት 30 ደቂቃ ቀደም ብለው በቦታው ይገኙ
 • በፈተናው ቦታ ያሉትን ምልክቶች ይመልከቱና ለፈተናው የተመደቡበትን ክፍል ይወቁ። ወደ ክፍሉ የሚገቡበት ሰአት ሲደርስ ተቆጣጣሪው ያሳውቅዎታል
 • ፕሮግራምዎትን በንፅህና ይያዙ። የተፈታኝ መለያ ቁጥርዎትን ወይንም ካንዲዴት ነምበር ይወቁ። በዚህ ቁጥርዎት መሰረት በተለየ የፈተና ክፍል እና ቦታ ይቀመጣሉ።

ፈተናውን በሚፈተኑበት ጊዜ

ወደ ፈተና ክፍል ሲገቡ፦

 • ማንኛውንም የመቀስቀሻ/የማስታወሻ ድምፅ ወይንም አላርም እና ተንቀሳቃሽ ስልክዎን ያጥፉ
 • በሰአትዎ ላይ የሚገኘውን መቀስቀሻ/ማስታወሻ ድምፅን ጨምሮ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ያጥፉ
 • ተንቀሳቃሽ ስልክዎንና ሌሎች ወደ ቦታው እንዳይገቡ የተከለከሉ ንብረቶችዎን (መጻሕፍት፣ ቦርሳዎች፣ ወዘተ . . .) ተቆጣጣሪው በሚያሳይዎት ቦታ ያስቀምጡ
 • ውሃ በኮዳ ይዘው መግባት ይችላሉ፤ ሆኖም ምንም አይነት ችግር እንዳይከሰት ከተቀመጡበት ወንበር አጠገብ መሬት ላይ ያስቀምጡት
 • ከተቀመጡ በኋላ ትክክለኛው ተፈታኝ እርስዎ መሆንዎን ለማረጋገጥ ተቆጣጣሪው ፓስፖርትዎን/መታወቂያዎትን እና ፕሮግራምዎትን እንዲያሳዩት ይጠይቅዎታል
 • ተቆጣጣሪው የጥያቄ ወረቀቶቹን ይሰጥዎታል (የተወሰኑ የመልስ መስጫ ወረቀቶችን እና/ወይም ባዶ ወረቀቶችን ሊሰጥዎትም ይችላል።)
 • በጥያቄ ወረቀቱ ላይ ስምዎ በትክክል ካልተፃፈ ወዲያውኑ ለተቆጣጣሪው ያሳውቁ
 • ተቆጣጣሪው እያንዳንዱን ወረቀት የሚመለከት ዝርዝር መመሪያ ይሰጣል። እባክዎ መመሪያውን በትኩረት ያዳምጡ፤ አሰራሩን የሚመለከት ምንም አይነት ጥያቄ ቢኖርዎት ተቆጣጣሪውን ይጠይቁ።

ፈተናው በሚጀምርበት ሰአት፦

 • በጥያቄው ወረቀት የፊተኛው ገፅ ላይ የሚገኘውን መመሪያ ያንብቡ (በመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይም መመሪያ ካለ ያንብቡ)
 • ተቆጣጣሪው ክፈቱ እስከሚል ድረስ የፈተና ወረቀቶቹን አይክፈቱ
 • ተቆጣጣሪው እያንዳንዱን የፈተና ወረቀት ለመስራት ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈቀድ ይናገራል። ለፈተናው መልስ ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ ስለማይሰጥዎት በተፈቀደው ጊዜ መሰረት መስራትዎትን እርግጠኛ ይሁኑ።
 • በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ላለው ጥያቄ መልስ ለመፃፍ መጠቀም የሚገባዎት እርሳስ ወይም እስክሪብቶ እንደሆነ ተቆጣጣሪው ያሳውቅዎታል።
 • መጻፍ፦ መልስዎን በጥያቄ ወረቀቱ ላይ በሚገኘው ግራጫ መስመር ውስጥ ይጻፉ። መልስዎን ለማሰብና ለማዘጋጀት ባዶ ወረቀቶቹን ይጠቀሙ።
 • ማዳመጥ፦ ፈተናው የተለያዩ ክፍሎች አሉት፤ በሲዲ የሚቀርበው ክፍል አስፈላጊ ቦታ ላይ እና ለተፈታኞች መመሪያ በሚሰጥበት ጊዜ በራሱ ይቆማል። እያንዳንዱ ክፍል ሁለት ጊዜ ይሰማል። መልስ ለመስጠት ጊዜ የሚሰጥዎት ሲሆን የፈተናው ሰአት ሲጠናቀቅ ከሲዲው ላይ ይሰማሉ።
 • ፈተናውን ከመፈተን እንዳይከለከሉ በፈተና ሰአት ከማውራት፣ ከመኮረጅ፣ እንዲገቡ የማይፈቀዱ እቃዎችን (እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ ነገሮችን) ከመያዝ ወይም ከመጠቀም ይቆጠቡ።
 • መፀዳጃ ቤት መሄድ ከፈለጉ ለፀጥታ ጉዳይ ሲባል የፈተናው ተቆጣጣሪ አብሮት ይሄዳል።
 • መፀዳጃ ቤት መሄድ ከፈለጉ እጅዎን ያንሱ። መፀዳጃ ቤት ለሄዱበት ተጨማሪ ጊዜ አይሰጥዎትም።
 • የመጻፍ ፈተናው ሊጠናቀቅ 10 እና 5 ደቂቃዎች ሲቀሩ ተቆጣጣሪው ያሳውቅዎታል።

ፈተናው ሲጠናቀቅ፦

 • ፈተናው ሲጠናቀቅ እስክሪብቶዎትን ወይም እርሳስዎትን እንዲያስቀምጡ ይጠየቃሉ
 • ከፈተናው ክፍል እንዲወጡ ከመፈቀዱ በፊት ተቆጣጣሪው የጥያቄ ወረቀቶችን፣ የመልስ ወረቀቶችን እና መልስዎን ለማሰብ የተጠቀሙባቸውን ወረቀቶች በሙሉ ይሰበስባል። እንዲህ በሚደረግበት ጊዜ ከመቀመጫዎት መነሳት የለብዎትም።

ከፈተና በኋላ

 • ከክፍሉ ከመውጣትዎት በፊት የግል ንብረቶችዎን በሙሉ መውሰድዎን ያረጋግጡ
 • የመናገር ፈተና ፕሮግራምዎትን መያዝዎን እርግጠኛ ይሁኑ። በፕሮግራምዎት ላይ ባለው መለያ ቁጥር ተጠቅመው ውጤትዎትን መመልከት ይችላሉ።

የተከሰቱ ነገሮች ካሉ ሪፖርት ማድረግ

 • ፈተናውን በአግባቡ መሥራት እንዳይችሉ የሚያግድዎት ነገር በፈተናው ሰአት ከተከሰተ (ለምሳሌ ከታመሙ ወይም በመስማት ፈተናዎት ወቅት ድምፅ ከረበሸዎት) ለትምህርት ቤቱ ተቆጣጣሪ/ለፈተናው ተቆጣጣሪ ወዲያውኑ ማሳወቅ ይገባዎታል።

በመናገር ፈተና ወቅት ምን ማድረግ ይገባል?

 • ፓስፖርትዎን/የቀበሌ መታወቂያዎትን ዋና ቅጂ እና ፕሮግራምዎትን ይዘው ይምጡ
 • ፈተናው ከሚጀምርበት ሰአት ቢያንስ 15 ደቂቃ ቀደም ብለው በቦታው ይገኙ
 • በፈተናው ቦታ ያሉትን ምልክቶች ይመልከቱና ለመናገር ፈተናው የተመደቡበትን ክፍል ይወቁ።
 • አስተባባሪው በመታወቂያዎት ላይ ያለውን ፎቶ በተፈታኞች ዝርዝር ላይ ካለው ፎቶ ጋር ያወዳድራል። ይህ ከተደረገ በኋላ ፈተናውን እስከሚፈተኑ ድረስ፣ ለመናገር ፈተና በተመደቡበት ቦታ ላይ መቆየት ይገባዎታል።
 • እባክዎ ፈተና ለመፈተን በሚጠብቁበት ሰአት ሌሎች ተፈታኞች እንዳይረበሹ ድምፅ አያሰሙ።
 • ስምዎት በትክክል እንዳልተፃፈ ካስተዋሉ ለአስተባባሪው ያሳውቁ፤ እርሱም ማስተካከያ እንዲደረግ ማስታወሻ ይይዛል።
 • ተንቀሳቃሽ ስልክዎን (እና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን) ያጥፉ። ንብረትዎትን አስተባባሪው በሚያሳይዎት ቦታ ላይ ያስቀምጡ።
 • የመናገር ፈተናው የሚሰጠው ለጥንድ ተፈታኞች ነው። የፈተናው ተቆጣጣሪ በተሰጠው ፕሮግራም ላይ ተመስርቶ ከየትኛው ተፈታኝ ጋር እንደተጣመሩ ያሳውቅዎታል።
 • የቀረ ሰው ካለ መዘግየት እንዳይኖር ሲባል የማጣመሩ ሥራ እንደገና ይካሄዳል።
 • የግልዎ ነጥብ መፃፊያ ወረቀት ይሰጥዎታል፤ ወረቀቱን እንዳያጥፉት፣ እንዳያጨማድዱት ወይም እላዩ ላይ እንዳይፅፉ ይጠንቀቁ። መፈተኛ ክፍሉ ውስጥ ሲገቡ ለፈታኙ ይስጡት።
 • ተፈታኞች በሚጣመሩበት ወቅት ተጣማሪ ያጣ ሰው ካለ ከሌሎች ጋር ሶስተኛ ሆኖ ይዳበላል። አንድ ተፈታኝ ለብቻው መፈተን አይችልም።

በፈተናው ቀን የሚነሱት ፎቶግራፍ

CAE, CPE እና BEC ፈተናዎችን የሚፈተኑ አመልካቾች ፈተና በሚወስዱበት ቀን ፎቶግራፍ ተነስተው እንዲያመጡ ይጠበቅባቸዋል። ተፈታኞች የመጻፍ ወይም የመናገር ፈተና በሚፈተኑበት ቀን ፎቶ መነሳት ይችላሉ።

ሁሉም አመልካቾች ወይም ወላጆች/አሳዳጊዎች በተገቢው የስምምነት ቅጽ ላይ (እዚህ ገጽ ላይ ያውርዱ) መፈረም ይኖርባቸዋል።