የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ፈተናዎችን ለመፈተን መመዝገብ የሚቻለው እንዴት ነው?

አመልካቾች ወደ አዲስ አበባ ብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ በአካል መጥተው የመረጡትን ፈተና ለመውሰድ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

ክፍያ የሚከናወንበት መንገድ

አመልካቾች የፈተናውን ክፍያ፣ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በየትኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በኩል ገንዘቡ ለብሪቲሽ ካውንስል እንዲከፈል ገቢ ማድረግ ይችላሉ።

በፈተናው ቀን የሚነሱት ፎቶግራፍ

የካምብሪጅ ኢንግሊሽ የቋንቋ ግምገማ ባወጣው ደንብ መሠረት፣ ለካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ Advanced (CAE) ለካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ Proficiency (CPE)፣ ለካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ Business (BEC) እና ለካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ Legal (ILEC) ፈተናዎች ለመውሰድ የሚመዘገቡ አመልካቾች የመናገር ፈተና ወይም የመጻፍ ፈተና በሚወስዱበት ቀን የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ መነሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ አመልካቾች በሙሉ በፈተና ቀን ፎቶግራፍ ተነስተው ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ያሏቸው ወላጆች/አሳዳጊዎች በፈተናው ዕለት ፎቶግራፍ ተነስቶ ማምጣት በሚለው አሠራር የማይስማሙ ቢሆን እንኳ እነዚህን አመልካቾች አሠራሩን ተከትለን እንመዘግባቸዋለን፤ ይሁን እንጂ የአመልካቹ ውጤት ሲመጣ ፎቶግራፍ እንደማይኖረው ከወዲሁ ማሳወቅ እንወዳለን።

ሁሉም አመልካቾች ወይም የአመልካች ወላጆች/አሳዳጊዎች በተገቢው የስምምነት ቅጽ ላይ (እዚህ ገጽ ላይ ያውርዱ) መፈረም ይኖርባቸዋል።  

ልዩ ዝግጅቶች

ለየት ያሉ ዝግጅቶች ማድረግ የሚቻለው በወረቀት ለሚሰጡ የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ፈተናዎች ብቻ ነው። ለእርስዎ የሚያስፈልጉትን ነገሮች እንዴት ልናመቻችልዎት እንደምንችል መረጃ ለማግኘትልዩ ዝግጅቶች የሚለውን ሊንክ ይመልከቱ። ለፈተናው በሚመዘገቡበት ወቅት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተሰጠዎትን የሕክምና ምሥክር ወረቀት ማቅረብዎ አስፈላጊ መሆኑን ልናስታውስዎት እንወዳለን።