እንዴት የአድቫንቴጅ አባል መሆን እችላለሁ?
የ ካምብሪጅ ኢንግሊሽ ተፈታኞችን እኛ ዘንድ በሚያስመዘግቡበት ጊዜ ወዲያውኑ ለአድቫንቴጅ አባልነት ይመዘገባሉ።
የአድቫንቴጅ አባል መሆን የሚያስገኛቸው ጥቅሞች
ከሚያገኟቸው ጥቅሞች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
- በኤሌክትሮ ማግኔቲክ ሞገዶች በሚሠሩ የጆሮ ማዳመጫዎች ወይም ዙሪያውን ባለ የድምፅ መስመር አማካኝነት የካምብሪጅ ኢንግሊሽ የማዳመጥ ፈተና ይሰጣል
- የካምብሪጅ ኢንግሊሽ የንግግር ፈተናን በመረጡት ቀን ይፈተናሉ
የምዝገባ ጊዜ በአምስት ቀናት ይራዘምልዎታል
- የግንኙነት ሥራ አስኪያጁ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታውን ይከታተላል
- በብሪቲሽ ካውንስል ኢኤልቲ ትምህርታዊ ስብሰባዎች ላይ ይጋበዛሉ
- የአድቫንቴጅ አባልነት ምሥክር ወረቀት፣ ፖስተሮች እና የመስኮት ስቲከሮች ያገኛሉ
- በትምህርት ቤትዎ እና በድረገፅዎት ላይ በሚገኙ ማስታወቂዎች ላይ የአድቫንቴጅን ምልክት የመጠቀም መብት ይኖርዎታል
በእያንዳንዱ ዓመት መጀመሪያ ላይ ስለ አባልነት ደረጃዎት እና የሚያገኟቸውን ጥቅሞች የሚመለከት የተሟላ መረጃ ይደርስዎታል።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ information@et.britishcouncil.org ላይ ይፃፉልን።