ትምህርት ቤታችሁ የብሪቲሽ ካውንስል ፈተናዎችን እንደሚፈትን ካርታ ላይ አሳዩ።
በመላው ዓለም ተቀባይነት ያላቸውን ሁለት የብቃት መመዘኛዎች ከሚያቀርቡ የተከበሩ የዩናይትድ ኪንግደም የፈተና ቦርዶች ጋር ልናገናኛችሁ እንችላለን። ሁለቱም የብቃት መመዘኛዎች ተማሪዎች የተሻለ ሥራ እና ተጨማሪ የትምህርት እድሎች እንዲያገኙ የሚረዱ ናቸው። የተማሪዎቻችሁ ስኬት ደግሞ ትምህርት ቤታችሁ መልካም ስም እንዲያተርፍ ያስችላል።
ፈተናዎች በጥሩ መልኩ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲካሄዱ በየደረጃው አስፈላጊውን ድጋፍ እና ምክር እንሰጣለን። አልፎ ተርፎም፣ ለአስተማሪዎች የሚጠቅሙ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ፕሮግራሞችን ማግኘት የምትችሉ ከመሆኑም በላይ ትምህርት ቤታችሁ በሌላ አገር ከሚገኝ ተቋም ጋር ትስስር መፍጠር ይችላል። ከዚህ በታች ባሉት ሊንኮች የበለጠ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።