ተማሪዎቻችሁ በመላው ዓለም የሚያገኙትን አጋጣሚ መጠቀም የሚያስችሉ ትምህርቶች እንዲያገኙ ትፈልጋላችሁ?
የA-ደረጃዎች ኮርስ፣ በዓለም አሉ ከሚባሉ እጅግ ግሩም እና ጠንከር ያሉ ትምህርቶች መካካል አንዱ እንደሆነ በመላው ዓለም በሚገኙ ቀጣሪዎች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ የታወቀ ነው። የA-ደረጃ ኮርሶችን የሚማሩ ተማሪዎች፣ ትምህርቶቹን በዝርዝር እየተማሩ እግረ መንገዳቸውን የፈጠራ ችሎታ እና ምክንያታዊ አስተሳሰብን እያዳበሩ ይሄዳሉ።
የA-ደረጃ ኮርሶች የእናንተን ተቋም በሚከተሉት መንገዶች ይረዳሉ፦
- በታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ትምህርቶች ማግኘት ያስችላሉ
- ብሩህ አእምሮ ያላቸውን ለስኬት የሚተጉ ተማሪዎች ያነቃቃሉ
- የተቋሙን ስም ይበልጥ ያሻሽላሉ
- ተማሪዎች ሌላ አገር ሄዶ መኖር የሚያስችል ብቃት እንዲኖራቸው ያስችላሉ
- ተማሪዎቻችሁ ጥሩ ሥራ ማግኘት እንዲችሉ ያስታጥቃቸዋል።