ከ14 እስከ 16 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ ተማሪዎቻችሁ ታዋቂ የሆነውን ዓለም አቀፋዊ ስልጠና እንዲያገኙ ትፈልጋላችሁ?

IGCSEs እና ኢንተርናሽናል GCSEs ኮርሶች፣ ለተማሪዎች አስደሳች አጋጣሚዎችን እንደሚከፍቱ በመላው ዓለም በሚገኙ ቀጣሪዎች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ የታወቀ ነው።

እነዚህ ስልጠናዎች የእናንተን ተቋም በሚከተሉት መንገዶች ይረዳሉ፦

  • ለስኬት የሚተጉ ተማሪዎችን ያነቃቃሉ
  • የተቋሙን ስም ይበልጥ ያሻሽላሉ
  • የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችን አካትተው ይዘዋል
  • ተማሪዎች ሌላ አገር ሄዶ መኖር የሚያስችል ብቃት እንዲኖራቸው ያስችላሉ
  • ተማሪዎችን ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት፣ ለሥራ ዓለም እና ለኑሮ ያዘጋጇቸዋል።

ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር እንዴት በሕብረት መሥራት እንደሚቻል እዚህ ይመልከቱ

አለም አቀፋዊ ስልጠና

ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) ያዘጋጀውን IGCSEs ከ160 በሚበልጡ አገራት የሚገኙ 9,000 ትምህርት ቤቶች ሲያስተምሩበት ፒርሰን ኤዴክሴል ያዘጋጀውን ኢንተርናሽናል GCSE ስልጠና ደግሞ ከ80 በሚበልጡ አገራት የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ይጠቀሙበታል። ብሪቲሽ ካውንስል ተቋማችሁን ከእነዚህ የፈተና ቦርዶች ጋር በማገናኘት ለተማሪዎቻችሁ ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና እንድትሰጡ ሊረዳችሁ ይችላል።

ኮርሱ

ብዙውን ጊዜ IGCSEs እና ኢንተርናሽናል GCSEs ኮርሶችን ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታት ይፈጃል። ተማሪዎች በጽሑፍ፣ በቃል እና በተግባር ፈተናዎች እንዲሁም በኮርሱ የሚሠሩ ሥራዎችን እየሠሩ ይገመገማሉ። 

የትምህርት ዓይነቶች መምረጥ

IGCSEs እና ኢንተርናሽናል GCSEs ኮርሶችን ከ70 በሚበልጡ የትምህርት ዓይነቶች ማግኘት ይቻላል፤ ኮርሶቹ ከሚያካትቷቸው መሰረታዊ የትምህርት ዓይነቶች መካከል ሒሳብ፣ እንግሊዝኛ፣ ሳይንስ እንዲሁም እንደ አካባቢያዊ አስተዳደር እና ዓለም አቀፋዊ እይታዎች የመሰሉ ልዩ ሙያዊ የትምህርት ዓይነቶች ይገኙባቸዋል።

ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች ከስምንት እስከ አስር የሚደርሱ የትምህርት ዓይነቶችን ለመማር ይመርጣሉ፤ ይህንን የሚወስነው ግን የወደፊት ግባቸው እና የአካባቢው የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ነው።

ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) የትኛውን የIGCSE ኮርስ ዓይነት እንደሚያዘጋጅ እዚህ ይመልከቱ

ፒርሰን ኤዴክሴል የትኛውን የኢንተርናሽናል GCSE የኮርስ ዓይነት እንደሚያዘጋጅ እዚህ ይመልከቱ።

የፈተና ቦርዶች

ፈተናዎችን የሚያዘጋጁት ሁለት ዋና ዋና የፈተና ቦርዶች ናቸው፤ እነርሱም፦ ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) እና ፒርሰን ኤዴክሴል ናቸው።

ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE)፣ IGCSEs ሲያዘጋጅ ፒርሰን ኤዴክሴል ደግሞ ኢንተርናሽናል GCSEs ያዘጋጃል።

ለእርስዎ ትምህርት ቤት የትኛው ቦርድ ቢሆን እንደሚሻል ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።

ደረጃዎች

መሰረታዊው የIGCSE ትምህርት መርሃ ግብር ከC እስከ G የሚደርስ ውጤት ያመጣሉ ተብለው ለሚጠበቁ ተማሪዎች ተስማሚ ነው። ከዚህ የሚሰፋው የትምህርት መርሃ ግብር ደግሞ ከA እስከ C የሚደርስ ውጤት ያመጣሉ ተብለው ለሚጠበቁ ተማሪዎች የሚሆን ይበልጥ ከበድ የሚል ይዘት አለው። 

ውጤቶች እና የነጥብ አሰጣጥ

ተማሪዎች በጽሑፍ፣ በቃል እና በተግባር ፈተናዎች እንዲሁም በኮርሱ የሚሠሩ ሥራዎችን እየሠሩ ይገመገማሉ። አንዳንድ ጊዜ ትምህርት ቤቶች ውጪ የተዘጋጁ ፈተናዎችን ብቻ ለመጠቀም ሊመርጡ አሊያም ደግሞ በኮርሱ የሚሠሩ ሥራዎችን እና ፈተናዎችን በአንድነት ለመጠቀም ሊመርጡ ይችላሉ።

 ውጤቶች የሚሰጡት በመላው ዓለም የታወቁትን ከ A* እስከ G ያሉትን ደረጃዎች በመጠቀም ነው። በኮርሱ የሚሠራው ሥራ እና የፈተና ወረቀቶች ሁሉ የሚታረሙት በዩናይትድ ኪንግደም ነው።

ውጤቶች

ተማሪዎች የመጨረሻውን ፈተና ከተፈተኑ ወይም ደግሞ የኮርሱን ሥራዎች ካስረከቡ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ፣ ለትምህርት ቤቶች ወይም ደግሞ በትምህርት ቤቶቹ አቅራቢያ ለሚገኝ የብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ ውጤቶች ይላካሉ።

ለፈተና መመዝገብ፦ ዋና ዋና ነጥቦች

  • ጊዜ ለመቆጠብ ተማሪዎቻችሁን በአንድ ላይ ማስመዝገብ ትችላላችሁ።
  • በኢንተርኔት ላይ ወይም ደግሞ የወረቀቱን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ማካሄድ ትችላላችሁ።
  • የመመዝገቢያ ጊዜው ከማብቃቱ በፊት መመዝገብ መቀጫ ከመክፈል ያድናል።
  • እናንተ አካባቢ ያለው የብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ ተማሪዎችን ለፈተና በመመዝገብ ሊረዳችሁ ይችላል።

የትምህርት ቤቶችን የአመዘጋገብ መመሪያ ቅደም ተከተል እዚህ ይመልከቱ።

ድጋፍ

ብሪቲሽ ካውንስል ተማሪዎችን ከመፈተን ጀምሮ የፈተና ወረቀቶችን በቦታው እስከ ማምጣት ድረስ ያሉትን ሁሉንም የፈተና ሂደቶች እናንተን ወክሎ ያከናውናል።

በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ እንድታገኙ እናደርጋለን፦

  • ቀደም ሲል የተሠሩ መመረቂያ ጽሑፎችን እና የልምምድ ፈተናዎችን
  • የእያንዳንዱን የትምህርት ዓይነት ዝርዝር መርሃ ግብሮች በሙሉ
  • ወቅታዊ የሆነውን የውጤት አሰጣጥን እና ሕግን የሚመለከት መረጃ
  • የፈታኞች ሪፖርቶችን እና አስፈላጊ ዜናዎችን

እንዲሁም ከትምህርት መመሪያዎች ጀምሮ በግል ለመማር እስከሚረዱ ድረ ገፆች ድርስ ያሉትን፣ ተማሪዎቻችሁ እንዲያጠኑ እና IGCSEs/ኢንተርናሽናል GCSEs ፈተናዎችን እንዲያልፉ መርዳት የሚያስችሏችሁን ሁሉንም የድጋፍ መስጫዎች እና ማስተማሪያዎች እንድታገኙ እናደርጋለን።

 በተጨማሪም ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ

  • A- እና AS-ደረጃዎችን ማስተማር ምን ጥቅም አለው?

ይህን ደግሞ ይመልከቱ