ትምህርት ቤታችሁ ባስመዘገባቸው ተማሪዎች ብዛት፣ ባገኘው የፈተና ውጤት እና በሚገኝበት ቦታ መሰረት የልዩ ስምምነቶች እና ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

ብሪቲሽ ካውንስል ከስልጠና እድሎች አንስቶ እስከ ስብሰባ መጋበዣ ትኬቶች መስጠት የሚደርሱ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ እውቀቶችን እና አዳዲስ ፕሮግራሞችን ማግኘት እንድትችሉ ይረዳችኋል።

ለምሳሌ ያህል፣ በቅርቡ ባዘጋጀነው የማበረታቻ ፕሮግራም በዓመት 5,000 ተማሪዎች ላስመዘገቡ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤቱ አስተማሪዎች እና የአመራር አካላት ለንደን ውስጥ በሚካሄደው ቤት (Bett) የተባለ የትምህርት ቴክኖሎጂ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ እድል ሰጥተናል።

በገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀው ይህ ጉብኝት፣ ተሳታፊዎች በዓለም እጅግ ከታወቁት አንዱ በሆነው በዚህ ትምህርታዊ ዝግጅት ላይ ከተደረጉት የትምህርት ቴክኖሎጂዎችን የሚመለከቱ ውይይቶች እና ትምህርታዊ ስብሰባዎች እውቀት መቅሰም አስችሏቸዋል። እንዲህ ያለው አጋጣሚ አዳዲስ ሃሳቦችን ወደ ትምህርት ቤታችሁ ለማስገባት እንዲሁም የትምህርት ቤታችሁን መልካም ስም እና የማስተማር ብቃት ለማሻሻል የሚያስችል ነው። ስድስት ቀን የሚፈጀው ይህ ጉብኝት ሁለቱን ዋና ዋና የፈተና ቦርዶቻችንን ማለትም ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስን (CIE) እና ፒርሰን ኤዴክሴልን መጎብኘትን ይጨምራል።

ባዘጋጀነው የማበረታቻ ፕሮግራም ላይ ስለ መመዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ information@et.britishcouncil.org አድራሻችን ላይ ይፃፉልን።