ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በሕብረት በመሥራት የመሻሻል ፍላጎት ካላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶችና ተቋሞች ጋር ዓለም አቀፋዊ በሆነ የትምህርት መረብ ታቀፉ።

ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በሕብረት በመሥራት በመላው ዓለም እውቅና ያተረፉትን የካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛምኔሽንስ (CIE) ወይም የፒርሰን ኤዴክሴልን ፈተናዎች መፈተን ትችላላችሁ። ይህም ለገጽታ ግንባታ የሚጠቅም ከመሆኑም ሌላ መልካም ስም ለማትረፍ ያስችላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተማሪዎች እዚያው በተማሩበት ቦታ ፈተና እንዲወስዱ ያስችላል። ከዚህ በተጨማሪ ከብሪቲሽ ካውንስልና ከፈተና ቦርዱ ጋር በመሆን የትምህርት ቤታችሁን ስም የማስተዋወቅ አጋጣሚ ታገኛላችሁ።

ብሪቲሽ ካውንስል ከዚህ በታች የተገለፁትን ድጋፎች ይሰጣል፦

  • በተደራጀ መንገድ ምዝገባ በማካሄድ መርዳት፣
  • ፈተና የመፈትን ሂደቱን መምራት፣
  • ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች ድጋፍና ምክር መስጠት፣
  • ሁሉም የፈተና ቦታዎች አስተማማኝ ጥበቃ የሚደረግላቸው መሆኑን ማጣራት፣
  • አስፈላጊ በሆኑባቸው ቦታዎች አስተማሪዎችንና ርዕሰ መምህራንን ለመርዳት በቦታው መገኘት።

ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር ሕብረት ለፈጠሩ ትምህርት ቤቶች ስለተደረጉት ልዩ ስምምነቶችና በሕብረት ለሚሠሩ ስለተዘጋጁ ፕሮግራሞች ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።

IGCSEs/ኢንተርናሽናል GCSEs መፈተን ምን ጥቅም አለው?

A- እና AS- ደረጃዎችን መፈተን ምን ጥቅም አለው?