IGCSE/ኢንተርናሽናል GCSE ወይም A-level የትምህርት ዓይነቶችን ሲመርጡ የፈተና ቦርድ የመምረጥ አጋጣሚም ይኖርዎታል። የፈተና ቦርዶች ለተማሪዎች የብቃት ማረጋገጫ የሚሰጡ ድርጅቶች ናቸው፤ ከዚህም ሌላ የፈተና ወረቀቶችን የማዘጋጀት፣ ፈተናውን የማረም እና ውጤት የመስጠት ሥራ ይሰራሉ። የትምህርት ቤት ፈተና ሲሆን ከሁለት ዓበይት ቦርዶች ጋር እንሠራለን፤ እነሱም ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) እና ፒርሰን ኤዴክሴል ናቸው።
ታዲያ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ የሚችሉት እንዴት ነው? ሁለቱም ቦርዶች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው እንዲሁም በመላው ዓለም በሚገኙ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት ያላቸው የብቃት ማረጋገጫዎች ይሰጣሉ።
ስለ እነዚህ ሁለት ቦርዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፦
- ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽን፡- IGCSEs
- ፒርሰን ኤዴክሴል:- ኢንተርናሽናል GCSEs
- ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ:- A-/AS-ደረጃዎች
- ፒርሰን ኤዴክሴል:- A-/AS-ደረጃዎች
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ የምሥክር ወረቀት ማግኘት ይፈልጋሉ?
IELTSን ጨምሮ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጋር በተያያዘ ስለሚሰጡ የምሥክር ወረቀቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።