በመላው ዓለም በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ቀጣሪዎች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው የብቃት ማረጋገጫዎች

የA-ደረጃዎች ኮርሶች፣ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጡ ትምህርቶች እና የሥራ ሙያ ሥልጠናዎች ላይ ለመካፈል በመስፈርትነት የሚጠየቁ በመላው ዓለም ተቀባይነት ያላቸው የብቃት ማረጋገጫዎች ናቸው። በአብዛኛው የA-ደረጃዎችን የሚማሩት በ17 እና በ18 ዓመት እድሜ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው። የA-ደረጃ ኮርሶች በሚከተሉት መንገዶች ሊረዱዎት ይችላሉ፦

  • ባሉበት አገር ወይም በውጪ አገር በሚገኝ ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ቦታ ማግኘት እንዲችሉ
  • የሚፈልጉትን ሥራ መጀመር እንዲችሉ
  • የሚወዱትን የትምህርት ዓይነት መምረጥ እንዲችሉ።

ለ A-ደረጃዎች እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል እዚህ ይመልከቱ። 

በዩኒቨርሲቲ የመረጡትን ኮርስ ለመውሰድ ምን እንደሚፈለግብዎት ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።

ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች የA-ደረጃዎችን ኮርሶች በሁለት ዓመታት ውስጥ ተምረው ያጠናቅቃሉ። በመጀመሪያው ዓመት፣ ግማሹን የA-ደረጃ ኮርስ ያጠናቅቃሉ፤ ይህም AS-ደረጃ ይባላል። በሁለተኛው ዓመት ደግሞ A2-ደረጃን ይማራሉ። በሁለቱ ዓመታት ያገኟቸው ውጤቶች ይቀናጁ እና A-ደረጃ ውጤት ያገኛሉ። በሁለቱም ዓመታት የወሰዷቸው የA-ደረጃዎች ኮርሶች በሚሠሩ ሥራዎች እና በፈተናዎች ይገመገማሉ (AS እና A2)።

A-ደረጃ ፈተናዎችን የሚያዘጋጁት ሁለት ዋና ዋና የፈተና ቦርዶች ናቸው፤ እነርሱም፦ ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) እና ፒርሰን ኤዴክሴል ናቸው። የሚማሩበት ትምህርት ቤት ወይም ኮሌጅ የመረጠው የፈተና ቦርድ ካለ እርስዎ መምረጥ ላያስፈልግዎት ይችላል።

ለእርስዎ የትኛው ቦርድ ቢሆን እንደሚሻል ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ። 

ባሉበት አገር የሚገኙትን የትምርት ዓይነቶች መሰረት በማድረግ እስከ 50 የሚደርሱ የA-ደረጃ ትምህርቶችን መምረጥ ይችላሉ። በእርስዎ አገር የሚገኙትን የትምህርት ዓይነቶች ለማወቅ ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) ድረ ገጽ ይመልከቱ።

በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአብዛኛው ተማሪዎች ሶስት የ A-ደረጃ የትምህርት ዓይነቶችን እንዲያድልፉ ይጠብቁባቸዋል፤ ይሁን እንጂ የመረጡት ዩኒቨርሲቲ የሚጠይቀውን የመግቢያ መስፈርት አስቀድመው ማወቅ ይኖርብዎታል።

በመረጡት ዩኒቨርሲቲ ቦታ ለማግኘት የሚያስፈልጉዎትን ደረጃዎች ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።

የትምህርት መመሪያዎችን፣ ቀደም ሲል የተሠሩ መመረቂያ ጽሑፎችን እና ሌሎች ጠቃሚ መማሪያዎችን እንዲያገኙ በማድረግ ትምህርትዎን መማር እና ፈተናዎችን ማለፍ እንዲችሉ ልንረዳዎት እንችላለን።

ለመማር የሚጠቅሙ ሃሳቦችን እና መንገዶችን እዚህ ይመልከቱ። 

በ A-ደረጃ የኮርስ ሥራዎች እና ፈተናዎች የተገኙት ውጤቶች A* እስከ E ያሉት ደረጃዎች ይሰጧቸዋል።

ተማሪዎች የመጨረሻውን ፈተና ከተፈተኑ ወይም ደግሞ የኮርሱን ሥራዎች ካስረከቡ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ፣ ለትምህርት ቤቶች ወይም ደግሞ በትምህርት ቤቶቹ አቅራቢያ ለሚገኝ የብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ ውጤቶች ይላካሉ።