በመላው ዓለም ተቀባይነት ያላቸው የብቃት ማረጋገጫዎች 

IGCSEs እና ኢንተርናሽናል GCSEs በመላው ዓለም ታዋቂ የሆኑ ከ14 – 16 ዓመት እድሜ ላይ ለሚገኙ ወጣቶች የተዘጋጁ የብቃት ማረጋገጫዎች ናቸው። በአገርዎ ወይም በውጪ አገር ከፍተኛ ትምህርት ወይም ልዩ የሙያ ትምህርት ለመማር መግቢያ በሮች ናቸው። ኮርሶቹ በሚከተሉት መንገዶች ሊረዱዎት ይችላሉ፦

  • ባሉበት አገር ወይም በውጪ አገር በሚገኝ ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ቦታ ማግኘት እንዲችሉ
  • የተሻሉ ሥራዎች ማግኘት እንዲችሉ
  • በሌላ አገር ለመኖር ወይም ለመማር የሚያስችሉዎትን የቋንቋ ፈተናዎች ማለፍ እንዲችሉ*
  • ይበልጥ አስደሳች እና ስኬታማ የሆነ ሕይወት እንዲመሩ የሚረዱዎትን ክህሎቶች ማዳበር እንዲችሉ።

*ለምሳሌ ያህል በ IGCSE የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና C ውጤት ማግኘት እንግሊዝኛ ተናጋሪ በሆኑ አገሮች በሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ በአብዛኛው ተቀባይነት ማግኘት ያስችላል። 

IGCSEs ለመማር እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል እዚህ ይመልከቱ። 

ኮርሱ የሚፈጀው ጊዜ እና የኮርሱ አወቃቀር

ብዙውን ጊዜ IGCSEs እና ኢንተርናሽናል GCSEs ኮርሶችን ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታት ይፈጃል። ግምገማው የጽሑፍ፣ የቃል እና የተግባር ፈተናዎችን እንዲሁም በኮርሱ የሚሠሩ ሥራዎችን ያካተተ ነው።

የፈተና ቦርዶች

ፈተናዎችን የሚያዘጋጁት ሁለት ዋና ዋና የፈተና ቦርዶች ናቸው፤ እነርሱም፦ ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) እና ፒርሰን ኤዴክሴል ናቸው። የሚማሩበት ትምህርት ቤት የፈተና ቦርድ መርጦ ሊሆን ይችላል።

የሚፈተኑት የካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) ፈተናን ከሆነ፣ IGCSEs ኮርስ ይማራሉ። የሚፈተኑት የፒርሰን ኤዴክሴልን ፈተና ከሆነ ደግሞ ኢንተርናሽናል GCSEs ይማራሉ።

ለእርስዎ ትምህርት ቤት የትኛው ቦርድ ቢሆን እንደሚሻል ለማቀቅ እዚህ ይመልከቱ። 

የትምህርት ዓይነቶች መምረጥ

ለእርስዎ የሚያስፈልገውን የ IGCSEs/ኢንተርናሽናል GCSEs ኮርስ የመምረጥ ነፃነት አለዎት። የመረጧቸው የትምህርት ዓይነቶች ወደፊት ሊሠሩት ካሰቡት ሥራ ወይም ሊማሩት ካሰቡት ትምህርት ጋር የሚጣጣሙ መሆን አለባቸው።

በእርስዎ አገር የሚገኙትን የትምህርት ዓይነቶች ለማወቅ ካምብሪጅ ኢንተርናሽናል ኤግዛሚኔሽንስ (CIE) ድረ ገጽ ይመልከቱ።

የአቅም ልዩነት

መሰረታዊው የIGCSE/ኢንተርናሽናል GCSE ትምህርት መርሃ ግብር ከC እስከ G የሚደርስ ውጤት ያመጣሉ ተብለው ለሚጠበቁ ተማሪዎች ተስማሚ ነው። ከዚህ የሚሰፋው የትምህርት መርሃ ግብር ደግሞ ከA እስከ C የሚደርስ ውጤት ያመጣሉ ተብለው ለሚጠበቁ ተማሪዎች የሚሆን ይበልጥ ከበድ የሚል ይዘት አለው።

መማር

የብሪቲሽ ካውንስልን GCSEPod፣ የፈተና ቦርዱን የትምህርት መመሪያዎችን፣ ቀደም ሲል የተሠሩ መመረቂያ ጽሑፎችን፣ ኢንተርኔት ላይ የሚገኙ ፕሮግራሞችን እና ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ለፈተና ለመዘጋጀት የሚያስችሉ መማሪያዎችን እንዲያገኙ ልንረዳዎት እንችላለን። 

ለመማር የሚጠቅሙ ሃሳቦችን እና ምክሮችን እዚህ ይመልከቱ።

ውጤቶች እና የነጥብ አሰጣጥ

ውጤቶች የሚሰጡት በመላው ዓለም የታወቁትን ከ A* እስከ G ያሉትን ደረጃዎች በመጠቀም ነው። በኮርሱ የሚሠራው ሥራ እና የፈተና ወረቀቶች ሁሉ የሚታረሙት በዩናይትድ ኪንግደም ነው።

ውጤትዎን የሚቀበሉት መቼ ነው?

የመጨረሻውን ፈተና ከተፈተኑ ወይም ደግሞ የኮርሱን ሥራዎች ካስረከቡ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ፣ ለትምህርት ቤትዎ ወይም ደግሞ በአቅራቢያ ለሚገኝ የብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ ውጤቶችዎ ይላካሉ።

ከዚህ በኋላስ?

IGCSE/ኢንተርናሽናል GCSE ኮርሶችን ተማሩ ማለት እንደ A- እና AS- ደረጃዎች ወይም ዩኒቨርሲቲ እንደ መግባት ያሉ ተጨማሪ የትምህርት እድሎችን ለማግኘት የመጀመሪያውን እርምጃ ወሰዱ ማለት ነው።

ይህን ደግሞ ይመልከቱ