ብሪቲሽ ካውንስል እንግሊዝኛ ቋንቋ መማር ለመጀመር ትክክለኛው ስፍራ ነው። በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎች፣ በትምህርት ቤቶቻችን የምንሰጣቸውን ኮርሶች በመከታተል ወይም ደግሞ ኢንተርኔት ላይ በነፃ የሚገኙ የአስተማሪዎች እና የተማሪዎች ፕሮግራሞችንበመጠቀም እንግሊዝኛ ቋንቋ እኛ ዘንድ ይማራሉ። በእንግሊዝኛ ቋንቋ ውጤታማ በሆነ መልኩ መግባባት እንዲችሉ የሚረዳዎትን ድፍረት እና ችሎታ እንዲያገኙ ልንረዳዎት እንችላለን። እንግሊዝኛ ቋንቋ በማስተማር ባካበትነው የ70 ዓመታት ልምድ ግብዎትን እንዲያሳኩ ልንረዳዎት እንችላለን።
ድረ ገጾቻችን አዋቂዎችን እና ልጆችን የሚያሳትፉ ሲሆን ለአስተማሪዎችም ትልቅ ድጋፍ ይሰጣሉ።
ይጎብኙ፦
ለርን ኢንግሊሽ
ብሪቲሽ ካውንስል ያዘጋጀውን ለርን ኢንግሊሽ ድረ ገጽ በመጠቀም በነፃ እንግሊዝኛን በኢንተርኔት ይማሩ። ችሎታዎችን ማዳበር የሚያስችሉ ጨዋታዎችን፣ ታሪኮችን፣ እየሰሙ የሚሠሯቸውን ሥራዎች እና የሰዋስው መልመጃዎችን እዚህ ድረ ገጽ ላይ ያገኛሉ።
በመስማት እና በማየት ክፍሉ ላይ በርካታ አዳዲስ እየሰሙ የሚሠሯቸውን ሥራዎች እና ቪዲዮዎች ማግኘት ይችላሉ፤ በንግድ እና በሥራ ክፍሉ ላይ ደግሞ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎትን በማሻሻል ያወጡት የሥራ ግብ ላይ መድረስ እንዲችሉ ለመርዳት የተዘጋጁ ፕሮግራሞችን ያገኛሉ። በተጨማሪም አዲስ የሰዋስው መማሪያ ክፍል እና አዲስ የIELTS ፈተና መለማመጃዎች አሉን።
በተለይ ለወጣት ተማሪዎች ታስበው የተዘጋጁ ፕሮግራሞችን ማግኘት ከፈለጉ እንግሊዝኛ መማሪያ ለልጆች ወይም እንግሊዝኛ መማሪያ ለወጣቶች የሚሉትን ድረገፆች መጎብኘት ይችላሉ።
ድረ ገጹ ላይ አስተያየትዎን ለማስፈር እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎትን በሚመለከት ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረብ እንዲችሉ አባል ይሁኑ።
በተጨማሪም እባክዎ የዜና አምዳችን እንዲደርስዎት ይመዝግቡ።
TeachingEnglish ቲቺንግ ኢንግሊሽ
ቲቺንግ ኢንግሊሽ ለአስተማሪዎች፣ ለአሰልጣኞች እና በሌሎች እንግሊዝኛ የማስተማር መስኮች ላይ ለተሰማሩ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ መመሪያ ነው።
በሁሉም የድረ ገጹ ክፍል ውስጥ፣ ከአጫጭር የሚሠሩ ነገሮች ጀምሮ እስከ ሙሉ የትምህርት ፕሮግራሞች ድረስ የልጆች እና የአዋቂዎች ማስተማሪያዎችን በነፃ ማውረድ ይችላሉ። እንዲሁም የተለያዩ የማስተማር ገፅታዎችን የሚገልፁ መረጃዎች፣ የመምህራን እውቀት ማጎልበቻዎች እና ማሰልጠኛዎች በነፃ ይገኛሉ።
ድረ ገጹ ላይ ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር አብሮ ለመሥራት፣ አስተያየትዎን ለማስፈር እና ለፈተና ለመዘጋጀት የሚረዱዎትን ነገሮች ለማውረድ ቲች ኢንግሊሽ ድረ ገጽ ላይ መመዝገብዎን አይዘንጉ። አባል ከሆኑ ከዚህ በታች ያሉትን ጥቅሞች ያገኛሉ፦
- የራስዎን መረጃ የሚያሰፍሩበት የግል አድራሻ ይኖርዎታል፤ እንዲሁም ዓለም አቀፉን የኢንተርኔት ማኅበረሰብ በአባልነት ይቀላቀላሉ
- ለተጋባዥ ጸሐፊዎቻችን፣ ለአስተማሪዎች እና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ጥያቄ መጻፍ ይችላሉ
- የአስተማሪዎች ማሰልጠኛዎችን በነፃ ያውርዱ
- አዳዲስ ነገሮችን ከሌሎች ቀድመው ያገኛሉ።
ለርን ኢንግሊሽ ሞባይል
ብሪቲሽ ካውንስል ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን ማሻሻል እንዲችሉ የሚረዱ በርካታ የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን አውጥቷል። በእነዚህ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች አማካኝነት፦
- በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎት የመስማት ችሎታዎን ማሻሻል እንዲችሉ የሚረዱዎትን በገሃዱ ዓለም የሚያጋጥሙ ውይይቶችን መስማት እና መመልከት ይችላሉ
- በፍላሽካርድ የቃላት መመዝገቢያ ፕሮግራም ላይ አዳዲስ ቃላትን መመዝገብ እና መማር ይችላሉ
- በአሳታፊ የሰዋስው ፕሮግራሞች በመጠቀም የሰዋስው ልምምድ ማድረግ ይችላሉ
- በቃላት ጨዋታ አማካኝነት ራስዎን እና ጓደኞችዎን መፈተን ይችላሉ።
- ልጆችን የፊደላት አነባበቦችን ማስተማር እና የልጆች ታሪኮችን በታብሌት እንዲያዩ ማድረግ ይችላሉ።
የብሪቲሽ ካውንስል የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ወጣት ተማሪዎችን ጨምሮ በሁሉም ደረጃ እና የእድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች ተስማሚ ናቸው። በ iTunes Store፣ በ Google Play፣ በ BlackBerry App World እና Windows Store ላይ ስለሚገኙት የኮምፒውተር ፕሮግራሞቻችን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ወይም ‘ብሪቲሽ ካውንስል’ ብለው በማሰስ ሁሉንም የኮምፒውተር ፕሮግራሞቻችንን ማግኘት ይችላሉ።