Cambridge English exams student
Your results ©

Credit Matt Wright

ውጤቶች

የአብዛኞቹ ፈተናዎች ውጤት የሚሰጠው የጽሑፍ ፈተናውን ከተፈተኑ ከአራት ሳምንታት በኋላ ነው። ሳይወጡ የቀሩ ውጤቶች ካሉ በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይሰጣሉ።

የግል ተፈታኞች

በአሁኑ ጊዜ ተፈታኞች በካምብሪጅ ኢንግሊሽ ላንጉጅ አሰስመንት በኢንተርኔት ውጤት መመልከቻ አገልግሎትአማካኝነት ውጤታቸውን በቀጥታ መመልከት ይችላሉ። የእያንዳንዱ ተፈታኝ የግል ፕሮግራም በዝርዝሩ ውስጥ የሚካተት ከመሆኑም በላይ ውጤት መሰጠት እንደጀመረ የሚገልፅ ኢሜይል ይላካል። ተፈታኞች ውጤታቸውን እስኪቀበሉ ድረስ ፕሮግራማቸውን ይዘው መቆየት እንዳለባቸው እባክዎ ያስታውሱ።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች

የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ላንጉዌጅ አሰስመንት ተፈታኞችን የሚመዘግቡ ትምህርት ቤቶች በሙሉ የተማሪዎቻቸውን ውጤት እና የውጤት ሪፖርትየትምህርት ቤቶች የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ላንጉዌጅ አሰስመንት ድረ ገፅላይ መመልከት ይችላሉ። ከምዝገባ በኋላ በዚህ የኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም መጀመር የሚያስችል ዝርዝር ሃሳቦችን የያዘ ኢሜይል ይደርስዎታል። በትምህርት ቤት በኩል የተመዘገቡ ተፈታኞችበኢንተርኔት ውጤት መመልከቻ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን መመዝገብ እንደሚችሉ እባክዎ ያስታውሱ።

ምሥክር ወረቀት

ፈተናውን ካለፉ፣ ውጤት ከወጣ በላ ባሉት ሁለት ወራት ውስጥ ምሥክር ወረቀት ይላክልዎታል። ምዝገባ ያካሄዱት በውጪ ቋንቋ ትምህርት ቤት በኩል ከሆነ ምሥክር ወረቀትዎ ለትምህርት ቤቱ ይላካል። ለፈተናው በግልዎ ተመዝግበው ከሆነ ደግሞ ምሥክር ወረቀትዎ በፖስታ ቤት አድራሻዎት ይላክልዎታል።

ወጣት ተማሪዎች

በእያንዳንዱ የፈተና ክፍል ላይ ማለትም በማዳመጥ፣ በማንበብ፣ በመጻፍና በመናገር ፈተናዎች ወቅት የሠሩትን ሥራ የሚያሳይ ሽልማት ከካምብሪጅ ኢንግሊሽ ላንጉዌጅ አሰስመንት ያገኛሉ።

ለእያንዳንዱ የፈተና ክፍል አንድ ወይም ከዚያ በላይ (እስከ አምስት የሚደርሱ) Cambridge shields ያገኛሉ፤ ይህም ማለት ከሁሉም ፈተናዎች በአጠቃላይ 15 Cambridge shields ማግኘት ይችላሉ። የወጣት ተማሪዎች ውጤት ፈተናውን በተፈተኑ በስምንት ሳምንታት ውስጥ ይወጣል። ፈተናውን አጠናቅቀው የሠሩ ሁሉ፣ ማድረግ የሚችሉትን ነገር የሚገልፅ (ማድረግ የማይችሉት ነገር አይገለፅም) ሽልማት ያገኛሉ። ሽልማቱ በፈተናው ላይ በመሳተፋቸው ምስጋና የሚቀርብበት ነው።

ኤክስቴንድድ ምሥክር ወረቀት

እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 2011 ጀምሮ ካምብሪጅ ኢንግሊሽ ኤክስቴንድድ ምሥክር ወረቀት መስጠት ጀምሯል፤ አላማውም ተፈታኞች የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ፈተና ሲፈተኑ ለታየው ተጨማሪ ችሎታቸው እውቅና መስጠት ነው። በተጨማሪም ዩኒቨርስቲዎች፣ አሠሪዎች እና ሌሎች ድርጅቶች የተፈታኞች ውጤት ከኮመን ዩሮፒያን ፍሬምወርክ ኦፍ ሬፈረንስ (ሲኢኤፍአር) ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መርዳት ነው።

ተጨማሪ መረጃ እና የናሙና ምሥክር ወረቀቶችን ለመመልከት ከዚህ በታች የተገለፁትን ድረ ገፆች ይመልከቱ፦

ውጤትን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ማቅረብ

ለተፈተኑት ፈተና የተሰጠዎት ውጤት ትክክል እንዳልሆነ ከተሰማዎት፣ ካምብሪጅ ኢንግሊሽ ጠንከር ያለና በጥንቃቄ የሚከናወን ውጤትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን የሚያስተናግድበት አሠራር አለው፤ በዚህ መንገድ ሁሉም የፈተናው ክፍሎች እንዲፈተሹና በሚቀርበው ጥያቄ መሰረት ውጤቱ እንዲስተካከል ይደርጋል። ስለ ውጤትዎ ጥያቄዎችን ማቅረብ የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን ማድረግ የሚችሉት በብሪትሽ ካውንስ በኩል ነው። እባክዎ ውጤትን የሚመለክት ጥያቄ ማቅረቢያ ቅፁን (ከዚህ ገፅ ላይ ዳውንሎድ አድርገው) ይሙሉ።

ውጤትን የሚመለከት ጥያቄ በሁለት ቅደም ተከተሎች ይከናወናል፦

ደረጃ ውጤትን የሚመለከት ጥያቄ የሚስተናገደው እንዴት ነው? ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል? ምን ያህል ይከፈላል?
ደረጃ 1 ቢሮ ውስጥ የሚካሄድ በድጋሚ የማጣራት ሥራ 5 ቀናት አካባቢ 35 ዩሮ ወይም ከዚህ ጋር የሚመጣጠን ብር
ደረጃ 2 የሁሉንም የጽሑፍ ፈተናዎች ውጤት የማስተካከል ሥራ* 5 ሳምንታት አካባቢ**

KET/PET: 100 ዩሮ ወይም ከዚህ ጋር የሚመጣጠን ብር

FCEfs/CAE/CPE: 130 ዩሮ ወይም ከዚህ ጋር የሚመጣጠን ብር

*ማንኛውንም የንግግር ፈተና የሚመለከት ጥያቄ በዚህ መልክ እንደማናስተናግድ እባክዎ ያስታውሱ።

**ተፈታኞች ደረጃ 2 ላይ የሚገኘውን ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉት ውጤት ከተቀበሉ እና ደረጃ 1 ላይ የሚገኘውን ውጤትን የሚመለከት ጥያቄ የማቅረብ ሂደት ካጠናቀቁ በኋላ ነው።