ተመላሽ ገንዘብ
ለፈተና የከፈሉትን ገንዘብ ተመላሽ የምናደርግልዎት ከህክምና ጋር በተያያዘ ምክንያት ብቻ ነው።
ምክንያትዎ ይህ ከሆነ ከመንግሥት ሆስፒታል የህክምና ምሥክር ወረቀት ማቅረብ አለብዎት (ከ IKA፣ TEBE፣ OAEE፣ EOPYY፣ ወዘተ . . . የሚቀርቡ የህክምና ምሥክር ወረቀቶችንም እንቀበላለን)፤ በተጨማሪም ተሰጥትዎት የነበረውን ደረሰኝ እና ተመላሽ ገንዘብ መጠየቂያ ቅፅ ሞልተው ማቅረብ ይኖርብዎታል።
ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች በማያያዝ የጽሑፍ ፈተና ከተሰጠበት ጊዜ በኋላ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ገንዘብ ተመላሽ እንዲደረግልዎ ለ ብሪቲሽ ካውንስል ጥያቄ ማቅረብ ይኖርብዎታል፤ ለሚያገኙት አገልግሎት ከከፈሉት ገንዘብ ውስጥ 75 በመቶው ተመላሽ ይደረግልዎታል።
ተቀባይነት ያገኙ የተመላሽ ገንዘብ ጥያቄዎች በሙሉ የሚስተናገዱት የፈተናው ውጤት ከወጣ በኋላ ነው።
የተፈፀሙ ክፍያዎችን ለቀጣይ ፈተናዎች ወይም ደግሞ ከአንድ የፈተና ደረጃ ወደ ሌላ የፈተና ደረጃ ማስተላለፍ አይቻልም።
ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግልዎት ሁሉንም ፈተናዎች (የወረቀት ፈተናዎች) ካልተፈተኑ ብቻ ነው።
ሌሎች ለውጦች
- ተፈታኞች የንግግር ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ወይም ሰአት እንዲቀየርላቸው መጠየቅ ይችላሉ። የንግግር ፈተናው ቀንና ሰአት እንዲቀየርልዎ ከፈለጉ ለ ብሪቲሽ ካውንስል ጥያቄዎን ያቅርቡ። ለፈተና ቦርድ ከሚከፈለው በተጨማሪ ቀንና ሰአት ለማስቀየር 65 የእንግሊዝ ፓውንድ ወይም ደግሞ ከዚህ ጋር የሚመጣጠን ብር ይከፈላል። እንዲህ ያሉ ለውጦችን ማድረግ የሚቻለው በዚያን ጊዜ ያለው የፈተና ወቅት እስከሚያበቃበት ድረስ ብቻ ነው፤ ይህም የሚሆነው የንግግር ፈተናው በአንድ የፈተና ክፍለ ጊዜ ከአንድ ጊዜ በላይ የሚሰጥ በመሆኑ ነው።
- የመጻፍና የማዳመጥ ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ (የፈተና ማእከል) ሊቀየር አይችልም።