ከIELTS ጋር የሚሠሩ አጋር ተቋሞችና የተቋሙ ተማሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ ያገኛሉ። የIELTS ፕሮግራም በራሳቸው ቦታ ለተማሪዎቻቸው ብቻ እንዲሰጥ ከሚፈልጉ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ የመሥራት ልማድ አለን። የተማሪዎቻችሁን አቅም መፈተን እንድትችሉ ሁሉንም ነገር ያካተተ የተሟላ ድጋፍ እናደርግላችኋለን።

የእኛ አጋር መሆን የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፦

  • ለዓመቱ ካዘጋጀነው ፕሮግራም ላይ ለእናንተ አመቺ የሆነውን የፈተና ቀን መምረጥ ትችላላችሁ፣
  • ተማሪዎቻችሁ በራሳችሁ ትምህርት ቤት ምንም ሳይጉላሉ ፈተናውን መውሰድ ይችላሉ፣
  • አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተማሪዎቻችሁ ለዝግጅት የሚረዱ የIELTSን መማሪያዎችና የትምህርት ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

የእኛ አጋር ለመሆን ወይም ለተጨማሪ መረጃ እባካችሁ በሚከተለው አድራሻ ጻፉልን፦ information@et.britishcouncil.org