IELTS ዓለም አቀፍ ፈተና ሲሆን በዓለም ዙሪያ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለመጓዝ ያስችላል። በመላው ዓለም የመንግሥት፣ የትምህርትና የሥራ ተቋሞችን ጨምሮ ከ8,000 በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች የትምህርት እድል ለመስጠት፣ ሥራ ለመቅጠርና የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት የIELTSን ውጤት ይቀበላሉ። የተማሪዎችን፣ የሠራተኞችን ወይም የዕጩ አመልካቾችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ለመመዘን ከፈለጋችሁ የIELTS ፈተና በቂ ነው።
የIELTS ፈተና የሚከተሉትን ለማከናወን አስተማማኝ መንገድ ነው፦
- በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተፈላጊው ደረጃ ላይ የሚገኙ ሠራተኞችንና ተማሪዎችን ለመመልመል።
- ተማሪዎቻችሁ ወደ ተለያየ የዓለም ክፍል መጓዝ ለሚጠይቁ ፕሮግራሞች ሲያመለክቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ደረጃቸውን ለመገምገም።
- ተማሪዎቻችሁ የመመረቂያ ጊዜያቸው ሲደርስ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለውን ዓለም አቀፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና እንዲወስዱ በማድረግ ማብቃት፤ ይህም በዛሬው ጊዜ ያለውን በፉክክር የተሞላ የሥራ ዓለም መቋቋም እንዲችሉ ይረዳቸዋል።
ለIELTS እውቅና የሚሰጥ ድርጅት መሆን
ለIELTS እውቅና የሚሰጥ ድርጅት ለመሆን በማመልከት እናንተ ጋ ሊያመለክቱ በሚችሉ ሰዎች ዘንድ ተቋማችሁ መልካም ስም እንዲኖረው አስተዋጽኦ ማድረግ ትችላላችሁ። በዚህ ጊዜ የድርጅታችሁ ስም IELTSን የሚቀበሉ በሚለው ሊንክ ላይ እና በሁሉም የIELTS ድረ ገጾች ላይ በነፃ ይወጣል፤ ይህም ድርጅታችሁ በዓለም ዙሪያ ፈተናውን ሊወስዱ በሚችሉ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ይሆናል።
በኢትዮጵያ የሚገኘውን ቡድናችንን ብታነጋግሩ እናንተን ለመርዳት ዝግጁ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለIELTS እውቅና የሚሰጥ ድርጅት ስለመሆን ያሏችሁን ጥያቄዎች ለመመለስ እጅግ ደስተኞች ናቸው።
ለአመልካቾች አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት እርዷቸው
በእናንተ ትምህርት ቤት ለመማር ማመልከት የሚፈልጉ ሰዎች ምን እንደምትጠብቁባቸው እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ የምትፈልጉትን የIELTS ውጤት ድረ ገጻችሁ ላይ እንድታወጡ እናበረታታለን። ይህም መረጃ ዕጩ አመልካቾች እናንተ ጋ ለማመልከት ወይም ላለማመልከት እንዲወስኑ ይረዳቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የማመልከት ሂደቱ ይበልጥ የተቀላጠፈ እንዲሆን የሚረዳ ከመሆኑም ሌላ ጥያቄ እንዳይበዛባችሁ ያደርጋል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የሥራ ባልደረቦቻችን ድረ ገጻችሁ ላይ ልታካትቱት የምትችሉትን ሕጋዊ የIELTS አርማ ሊሰጧችሁ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባካችሁ የIELTS ጉዳይ የሚመለከታቸውን የቡድን አባላት አነጋግሩ።
ዝርዝር መረጃ ለማግኘት አባክዎ IELTS guide for prospective recognising organisations የሚለውን ከኢንተርኔት ላይ Download ያድርጉ።