የስራዎን እድገት ለማፍጠን፣ ለተጨማሪ ትምህርት ለመዘጋጀት ወይም ለመግባባት የሚያስችልዎን እንግሊዝኛ ቋንቋ ለማሳደግ ብቃት ካላቸው ተማሪዎቻችን ጋር ይማሩ። አላማዎ ምንም ይሁን የሚፈልጉት አላማ እንዲሳካልዎ በስልጠናችን ውስጥ ሁሉንም ጥረት እናደርጋለን።
ወደ ግቦችዎ አንድ እርምጃ የሚያቀርብዎት አነቀቃቀቂ ኮርስ
MyClass ወደ ግቦችዎ እንዲቀርቡ ይረዳዎታል፡፡ በተጨማሪም ለእርስዎ ወሳኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንግሊዝኛን ለመጠቀም ራስ መተማመንዎን ያሳድግሎታል። ክፍሎቻችን የእንግሊዝኛ ቋንቋን በተሻለ ሁኔታ እንዲጠቀሙ በማነሳሳት ባለሙያዊ ስልጠና በሚሰጡ ከፍተኛ ብቃት ባላቸው መምህራን ይመራሉ።
የመማር ዓላማዎ ምንም ይሁን ምን ፣ ለስራ ቦታ ሆነ ለማህበራዊ ተግባቦቶች ወይም ሁለቱንም፤ እኛ እናግዝዎታለን። ለእርስዎ በሚመችዎት ጊዜ ትምህርትዎን እና ጥናትዎን ማስተካከል ይችላሉ።
ምን እንደሚማሩ አስቀድመው ይወቁ
እያንዳንዱ የMyClass ክፍለ ጊዜ የ90 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው በውስጡም የመናገር፣ የመጻፍ፣ የማንበብ እና የመስማት ክህሎቶችን የያዘ ነው።. በሁሉም ክፍለ ጊዜ አዲስ ቃላትን፣ ሃረጋትን እንዲሁም የቃላት አነጋገር፣ ሰዋሰው እና ትክክለኛ አጠቃቀምን ይማራሉ።
በእያንዳንዱ ኮርስ ነባራዊውን አለም የሚያንጸባርቁ ሁኔታዎችን በእንግሊዝኛ ይለማመዳሉ፡፡ እናም ግቦችዎን ለማሳካት የቋንቋ እና በቀን ለቀን ህይወትዎ አስፈላጊ የሆኑ ችሎታዎችን ይቀስማሉ።
የስልጠና ቆይታዎን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ተመሳሳይ ደረጃ ካላቸው ተማሪዎች ጋር ይማራሉ። የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠናዎቻችን ከአውሮፓ የማመሳከሪያ መዋቅር ጋር የሚዛመድ ነው። (CEFR).
በእንግሊዘኛ ችሎታዎ ላይ ተመስርተው የተደራጁ የትምህርት ገጽታዎች
የሥራ ቦታ እንግሊዝኛ - እንግሊዝኛዎን በተለመዱ የሥራ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት እንደሚጠቀሙ ለማለማመድና ክህሎቶችን ለማዳበርእንዲረዳ የተነደፈ።
ለማህበራዊ ተግባቦት የሚጠቅም እንግሊዝኛ - እንግሊዝኛን በበለጠ በራስ መተማመን እንዲናገሩ ለማገዝ የተለያዩ ርዕሶችን እና ማህበራዊ ሁኔታዎችን ያካተተ ነው ።
የቋንቋ ችሎታዎን ያሻሽሉ፣ ስሜቶችን እና አስተያየቶችን እንዴት መግለፅ እንደሚችሉ ይማሩ ወይም አዳዲስ ትምህርቶችን ያስሱ! ስለፍላጎቶችዎ - ስፖርት፣ጉዞ፣አካባቢያዊ ጉዳዮች፣የሕይወት ክስተቶች ወዘተ ለመወያየት ይፈልጉ ይሆናል። ምናልባት ወደፊት የሚሆነውን ለመገመት ፣አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወይም የአየር ንብረት ለውጥን ማሰስ ይፈልጉይሆናል። ለሁሉም አመቺ የሆነውን ኮርሳችንን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡