ፍፁም ስለመሆን አይደለም እያወራን ያለነው፡፡ ይልቁንም ስለ እድገት ነው። የሕይወት ግቦችዎን ለማሳካት በሚጓዙበት መንገድ ላይ  እያንዳንዱ እርምጃዎን ከእርስዎ ጎን ሆነን በትክክለኛው ሀዲድ እንዲሄዱ እናግዝዎታለን።

ከእኛ ጋር በተመሳሳይ መንገድ ይጓዙ

አላማዎን ለማሳካት በየጊዜው ለውጥ ማሳየት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንረዳለን። መምህሮቻችን በመደበኛ ስልጠና እና በመመዘኛ ፈተናዎች ወቅት እጅግ ጠቃሚ ምክሮችን ይሰጡዎታል።

ማንኛቸውንም አራት ትምህርቶች ሲያጠናቅቁ የትምህትዎን ሂደት እንዴት እንደሆነ መጠየቅ ይችላሉ - የ MyClass ድረ ገጽ (website) ወይም  መተግበሪያን (app) በመጠቀም በዋናዎቹ የትምህርት ውጤቶችዎ ላይ አስተማሪዎ የሰጥዎትን ግብረመልሶች የመገምገም ዕድል ይኖርዎታል።

በበይነ መረብ (online) በራስዎ እንዲያጠኑ እና ስለራስዎ እንዲያውቁ የሚረዱ መልመጃዎች በመስራት ትምህርትዎን ከመማሪያ ክፍል ባሻገር ከህይወትዎ ጋር ያዋህዱት፡፡ ከእያንዳንዱ ትምህርት ክፍለ ጊዜ በኋላ አስተማሪዎ የተማሩትን እንዲገመግሙ ያበረታታዎታል።