ከብሪቲሽ ካውንስል የፈተና ውጤትዎን ያለ ምንም ችግር በፍጥነት ያግኙ።

የፈተና ውጤቴን የማገኘው መቼ ነው?

በአብዛኛው ፈተና ከተፈተኑ ከስድስት ሳምንት በኋላ ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ። የፈተና ውጤትዎን ካርድ ከብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ መውሰድ ይችላሉ። 

የፈተና የምሥክር ወረቀቴን ማግኘት የምችለው መቼ ነው?

በአብዛኛው ጊዜያዊ ውጤት ከወጣ በኋላ ባሉት ከ9 እስከ 10 ሳምንታት ውስጥ የምሥክር ወረቀቶች ተዘጋጅተው ይጠናቀቃሉ።

ያገኙት ውጤት እንደጠበቁት ባይሆንስ?

የተሻለ ውጤት ለማግኘት ጠብቀው ከነበረ ወይም የመረጡት ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ለመግባት የሚያስፈልገውን ውጤት ካላመጡ አይደናገጡ። ፈተናውን በድጋሚ የመውሰድ አጋጣሚ ያለዎት ከመሆኑም ሌላ በአንዳንድ ሁኔታዎች የፈተና ውጤቱ እንዲስተካከልልዎት መጠየቅ ይችላሉ። በድጋሚ ስለመፈተንና ውጤት ስለማስተካከል የቀረበውን መረጃ እዚህ ይመልከቱ።