ገና አዲስ ጀማሪም ይሁኑ እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፈው መናገር የሚችሉ እና ችሎታዎን ማሻሻል የሚፈልጉ፣ ተማሪም ይሁኑ ባለሙያ ለእርስዎ የሚመጥን ፈተና አለን። ከጀነራል ኢንግሊሽ ብቃቶች መካከል ለእርስዎ የሚመጥነው የትኛው እንደሆነ ይወቁ።

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ - ኪ (KET) እና ኪ ፎር ስኩልስ (KETfS)

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ - ኪ በሌላ አነጋገር ኪ ኢንግሊሽ ቴስት (KET) ተብሎም ይጠራል። ይህ በካምብሪጅ ኢንግሊሽ ከታቀፉት ውስጥ ዝቅተኛው ደረጃ የጀነራል ኢንግሊሽ ፈተና ነው። ፈተናው በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ከሚያጋጥሙ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ በመሠረታዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመግባባት ችሎታ እንዳለዎት ለማረጋገጥ ያስችላል።

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ ኪ ፎር ስኩልስ (KETfS)፣ ከካምብሪጅ ኢንግሊሽ - ኪ ጋር እኩል ደረጃ ያለው ከመሆኑም ሌላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ተመሳሳይ ዓይነት የምሥክር ወረቀት ለማግኘት ያስችላል። በሁለቱ መካከል ያለው ብቸኛው ልዩነት የዚህ ፈተና ይዘት ተማሪ በሆኑ ልጆች ፍላጎትና ልምድ ላይ የሚያተኩር መሆኑ ነው።

ሌቭል ኦፍ ኩዋሊፊኬሽን - ኤለመንተሪ = A2 በ ኮመን ዩሮፒያን ፍሬም ወርክ ሲታይ።

ይህ ፈተና የተዘጋጀው ለእነማን ነው?

እንግሊዝኛ ቋንቋ ለ250 ሰዓት ገደማ ከተማሩ ወይም ልምምድ ካደረጉ እንዲሁም መሠረታዊ የሆነ እንግሊዝኛ የመናገር፣ የመጻፍና የመረዳት ችሎታ ካለዎት KET ሊያመልጥዎት አይገባም። ይህ ፈተና ወደፊት ለሥራ ወይም ለትምህርት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እያዳበሩ ለመሄድ የሚወስዱት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ይህን ፈተና ለመፈተን ቀጥሎ የተገለፁትን ነገሮች ማድረግ መቻል ይኖርብዎታል፦

●      ስለ ራስዎም ሆነ ስለ ሌሎች ሰዎች ጥያቄዎች መጠየቅና መልስ መስጠት፣

●      ሰዎች ረጋ ብለውና አጥርተው የሚናገሩትን ማስታወቂያና መመሪያ መረዳት፣

●      ስላነበቡት ወይም ስለሰሙት ነገር ያለዎትን አስተያየት ለሌሎች መግለጽ።

የፈተናው ይዘት ምን ይመስላል?

ፈተናው ሦስት ክፍሎች አሉት። የማንበብ፣ የመጻፍና የማዳመጥ ፈተናዎችን በአንድ ቀን ውስጥ ተፈትነው ያጠናቅቃሉ። የመናገር ፈተናውን ለመፈተን ደግሞ ሌላ ቀን መምጣት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለመናገር ፈተናው የሚቀመጡት ከሁለት ፈታኞችና ከአንድ ሌላ ተፈታኝ ጋር ነው።

KET / KETfS ማንበብ እና መጻፍ ማዳመጥ መናገር 
የሚፈቀደው ጊዜ 1 ሰዓት ከ10 ደቂቃ 30 ደቂቃ ከ8-10 ደቂቃ ለሁለት ተፈታኞች በጋራ
አጠቃላይ ውጤት (በመቶኛ) 50% 25% 25%

Cambridge English: Preliminary (PET) and Preliminary for Schools (PETfS)

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ - ፕሪሊሚነሪ በሌላ አነጋገር ፕሪሊሚነሪ ኢንግሊሽ ቴስት (PET) እና ፕሪሊሚነሪ ኢንግሊሽ ቴስት ፎር ስኩልስ (PETfS) ተብሎም ይጠራል። ይህ ፈተና በተጨባጭ በዕለት ተዕለት ሕይወት በሚያጋጥሙ ሁኔታዎች ወቅት በእንግሊዝኛ የመግባባት ችሎታ እንዳለዎት ለማወቅ ያስችላል። ፈተናው፣ ለአንድ ዓይነት ሙያ የሚጠቅም እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመማር የሚጠበቀውን ብቃት ለማሟላት የሚፈልጉ ከሆነ ጥሩ መሠረት ይሆንልዎታል።

ሌቭል ኦፍ ኩዋሊፊኬሽን - ኢንተርሚዲየት = B1 በ ኮመን ዩሮፒያን ፍሬም ወርክ ሲታይ።

ይህ ፈተና የተዘጋጀው ለእነማን ነው?

PET ለመፈተን ትምህርቱን መከታተልዎ፣ ከአገር አገር ሲጓዙ ወይም በሥራ ጉዳይ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር ሲገናኙ መግባባት እንዲችሉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎን እንዲሻሽሉ ይረዳዎታል።

ይህን ፈተና ለመፈተን ቀጥሎ የተገለፁትን ነገሮች ማድረግ መቻል ይኖርብዎታል፦

  • ስለሚወዱትና ስለሚጠሉት ነገር ለሌሎች መግለጽና በዚያ ዙሪያ መወያየት፣
  • በቃል እና በጽሑፍ የሚቀርቡ ማስታወቂያዎችንና መመሪያዎችን መረዳት፣
  • ደብዳቤ መጻፍ አሊያም ስብሰባ ላይ ወይም ውይይት ሲካሄድ ማስታወሻ መያዝ።

ፈተናው የሚሰጠው እንዴት ነው?

ፈተናው ሦስት ክፍሎች አሉት። የማንበብ፣ የመጻፍና የማዳመጥ ፈተናዎችን በአንድ ቀን ውስጥ ተፈትነው ያጠናቅቃሉ። የመናገር ፈተናውን ለመፈተን ደግሞ ሌላ ቀን መምጣት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለመናገር ፈተናው የሚቀመጡት ከሁለት ፈታኞችና ከአንድ ሌላ ተፈታኝ ጋር ነው።

PET / PETfS ማንበብ እና መጻፍ ማዳመጥ መናገር 
የሚፈቀደው ጊዜ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 30 ደቂቃ ከ10-12 ደቂቃ ለሁለት ተፈታኞች በጋራ
አጠቃላይ ውጤት (በመቶኛ) 50% 25% 25%

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ ፈርስት ሰርቲፊኬት ኢን ኢንግሊሽ (FCE) እና ፈርስት ሰርቲፊኬት ኢን ኢንግሊሽ ፎር ስኩልስ (FCEfS)

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ - ፈርስት በሌላ አነጋገር ፈርስት ሰርቲፊኬት ኢን ኢንግሊሽ (FCE) እና ፈርስት ሰርቲፊኬት ኢን ኢንግሊሽ ፎር ስኩልስ (FCEfS) ተብሎም ይጠራል። ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጋር በተያያዘ ይህን ብቃት ማግኘትዎ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በሚነገርበት ቦታ ለመሥራት ወይም ለመማር የሚያስፈልገው፣ እንግሊዝኛ የመናገር እና የመጻፍ በቂ ችሎታ እንዳለዎት ያሳያል።

ሌቭል ኦፍ ኩዋሊፊኬሽን - አፐር ኢንተርሚዲየት = B2 በ ኮመን ዩሮፒያን ፍሬም ወርክ ሲታይ።

ይህ ፈተና የተዘጋጀው ለእነማን ነው?

እንግሊዝኛ ቋንቋ በሚነገርበት ቦታ መሥራት፣ እንግሊዝኛ በሚነገርበት አገር መኖር ወይም በእንግሊዝኛ የሚሰጥ መሠረታዊ ትምህርት ወይም የቅድመ ዩኒቨርሲቲ ኮርስ መከታተል የሚፈልጉ ከሆነ FCE መማር ይኖርብዎታል።

ይህን ፈተና ለመፈተን ቀጥሎ የተገለፁትን ነገሮች ማድረግ መቻል ይኖርብዎታል፦

  • አጠር ያለ ሪፖርትና ኢሜይል መጻፍ፣
  • በእንግሊዝኛ አንድን ሐሳብ መግለጽ ወይም ሰፋ ያለ ውይይት ማድረግ፣
  • በቲቪ እና በጋዜጦች ላይ በእንግሊዝኛ የሚቀርብን ርዕሰ ጉዳይ መረዳት።

ፈተናው የሚሰጠው እንዴት ነው?

FCE ፈተና አምስት ክፍሎች አሉት። የማንበብ፣ የመጻፍና የማዳመጥ ፈተናውን በአንድ ቀን ውስጥ ተፈትነው ያጠናቅቃሉ። የመናገር ፈተናውን ለመፈተን ደግሞ ሌላ ቀን መምጣት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለመናገር ፈተናው የሚቀመጡት ከሁለት ፈታኞችና ከአንድ ሌላ ተፈታኝ ጋር ነው።

 FCE / FCEfs ማንበብ መጻፍ በእንግሊዝኛ መጠቀም ማዳመጥ መናገር
የሚፈቀደው ጊዜ 1 ሰዓት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ 45 ደቂቃ 40 ደቂቃ 14 ደቂቃ 
አጠቃላይ ውጤት (በመቶኛ) 20% 20% 20% 20% 20%

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ አድቫንስድ (CAE)

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ - አድቫንስድ በሌላ አነጋገር ካምብሪጅ አድቫንስድ ሰርቲፊኬት ኢን ኢንግሊሽ (CAE) ተብሎም ይጠራል። ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጋር በተያያዘ እዚህ ብቃት ላይ ከደረሱ፣ በንግድ ሙያ ከተሰማራ ሰው ወይም የድኅረ ምረቃ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆነ ሰው የሚጠበቀው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ አለዎት ማለት ነው።

ሌቭል ኦፍ ኩዋሊፊኬሽን - አድቫንስድ = C1 በኮመን ዩሮፒያን ፍሬም ወርክ ሲታይ።

ይህ ፈተና የተዘጋጀው ለእነማን ነው?

ከሥራና ከከፍተኛ ትምህርት ጋር በተያያዘ ያለ ችግር መግባባት እንደሚችሉ ለአሠሪዎች ወይም ለዩኒቨርሲቲዎች ማሳየት ከፈለጉ CAE ፈተና መውሰድ ይኖርብዎታል። ይህን ፈተና ለመፈተን ቀጥሎ የተገለፁትን ነገሮች ማድረግ መቻል ይኖርብዎታል፦

●      ውስብስብ ይዘት ያላቸው ሪፖርቶችና ኢሜይሎች መጻፍ እንዲሁም ስብሰባ ሲካሄድ ወይም ንግግር ሲሰጥ ማስታወሻ መያዝ፣

●      ውስብስብ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ንግግር ማቅረብ፣

●      ልብ ወለድ መጻሕፍትም ሆነ ጋዜጦች ላይ የሚወጡ በተለያየ ጉዳይ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶችን መረዳት መቻል።

ፈተናው የሚሰጠው እንዴት ነው?

CAE ፈተና አምስት ክፍሎች አሉት። የማንበብ፣ የመጻፍና የማዳመጥ ፈተናውን በአንድ ቀን ውስጥ ተፈትነው ያጠናቅቃሉ። የመናገር ፈተናውን ለመፈተን ደግሞ ሌላ ቀን መምጣት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለመናገር ፈተናው የሚቀመጡት ከሁለት ፈታኞችና ከአንድ ሌላ ተፈታኝ ጋር ነው።

  ማንበብ መጻፍ በእንግሊዝኛ መጠቀም ማዳመጥ መናገር
የሚፈቀደው ጊዜ ሰዓት ከ15 ደቂቃ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 1 ሰዓት 40 ደቂቃ 15 ደቂቃ ለሁለት ተፈታኞች በጋራ
አጠቃላይ ውጤት (በመቶኛ) 20% 20% 20% 20% 20%

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ፦ ፕሮፊሸንሲ (CPE)

ካምብሪጅ ኢንግሊሽ - ፕሮፊሸንሲ በሌላ አነጋገር ካምብሪጅ ሰርቲፊኬት ኦፍ ፕሮፊሸንሲ ኢን ኢንግሊሽ (CPE) ተብሎም ይጠራል። እዚህ ብቃት ላይ ከደረሱ እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፈው መናገር እንደሚችሉ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ በምርምር፣ በትምህርት እና በሙያዊ ተቋማት ውስጥ አለምንም ችግር በእንግሊዝኛ ሥራ ማከናወን ይችላሉ ማለት ነው። ይህ ከፍተኛው የካምብሪጅ ኢንግሊሽ የብቃት ማረጋገጫ ነው።

ሌቭል ኦፍ ኩዋሊፊኬሽን - ፕሮፊሸንት = C2 በ ኮመን ዩሮፒያን ፍሬም ወርክ ሲታይ።

ይህ ፈተና የተዘጋጀው ለእነማን ነው?

ለከፍተኛ የሥራ አመራር የሚመጥን እንግሊዝኛ መናገር እንደሚችሉ ለአሠሪዎች ማሳየት ከፈለጉ አሊያም በድኅረ ምረቃ ወይም በዶክትሬት ደረጃ በእንግሊዝኛ በሚሰጥ ዩኒቨርሲቲ መማር ከፈለጉ CPE ፈተና መውሰድ ይኖርብዎታል።

ይህን ፈተና ለመፈተን ቀጥሎ የተገለፁትን ነገሮች ማድረግ መቻል ይኖርብዎታል፦

●      በእንግሊዝኛ የሚሰሙትን ወይም የሚያነቡትን ነገር ሁሉ መረዳት፣

●      መደበኛ፣ የትምህርትና ፈሊጣዊ አነጋገሮችን መጠቀም እና መረዳት፣

●      ውስብስብ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ ባሉ አወዛጋቢ ጉዳዮች ዙሪያ መደራደር፣ መከራከርና መወያየት።

ፈተናው የሚሰጠው እንዴት ነው?

CPE ፈተና አራት ክፍሎች አሉት። የማንበብና እንግሊዝኛ የመጠቀም፣ የመጻፍና የማዳመጥ ፈተናዎችን በአንድ ቀን ውስጥ ተፈትነው ያጠናቅቃሉ። የመናገር ፈተናውን ለመፈተን ደግሞ ሌላ ቀን መምጣት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለመናገር ፈተናው የሚቀመጡት ከሁለት ፈታኞችና ከአንድ ሌላ ተፈታኝ ጋር ነው።

 CPE ማንበብና በእንግሊዝኛ መጠቀም መጻፍ ማዳመጥ መናገር
የሚፈቀደው ጊዜ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 40 ደቂቃ 16 ደቂቃ ለሁለት ተፈታኞች በጋራ
አጠቃላይ ውጤት (በመቶኛ) 40% 20% 20% 20%

በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ላንጉዌጅ አሰስመንት ፈተና መውሰድ

በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ላንጉዌጅ አሰስመንት ፈተና ለመውሰድ ይመዝገቡ።

በኢትዮጵያ የካምብሪጅ ኢንግሊሽ ላንጉዌጅ አሰስመንት ፈተና መቼ እና የት እንደሚሰጥ እንዲሁም ክፍያው ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ መረጃዎቹን ይመልከቱ።

በፈተና ቀን ምን መጠበቅ ይኖርብዎታል?

በወረቀት የተሠሩ ፈተናዎች ውጤት ፈተናውን ከወሰዱ በኋላ ባሉት ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ ይወጣል፤ በኮምፒውተር የተሠሩ ፈተናዎች ውጤት ደግሞ ፈተናውን ከወሰዱ በኋላ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይወጣል።

ብሪቲሽ ካውንስልን መምረጥ ምን ጥቅም አለው?