ቲቺንግ ኖውሌጅ ቴስት (TKT) ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን እንግሊዝኛ ቋንቋ በማስተማሩ ሥራ የተሳካልዎት እንዲሆኑ የሚያስፈልገው ችሎታ እንዳለዎት የሚፈተኑበት ነው። ፈተናው በሁሉም ዕድሜ ላይ ለሚገኙ እና የተለያየ ችሎታ ላላቸው አስተማሪዎች የሚመጥን ነው። ፈተናው የተለያዩ ክፍሎች አሉት።
ይህን ፈተና መፈተን የሚችለው ማን ነው?
TKT በመፈተን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ቋንቋ የማስተማር ችሎታ እንዳለዎት የሚያሳይ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት ይችላሉ። በራስ የመተማመን ስሜትዎንና ችሎታዎትን ማሳደግ የሚፈልጉ አዲስ አስተማሪ ቢሆኑ ወይም ደግሞ አንድ የተለየ ሙያ እንዲኖርዎት ፍላጎት ያለዎት ልምድ ያካበቱ አስተማሪ ቢሆኑ አሊያም እንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር ገና የጀመሩ ቢሆኑም ይህ የብቃት ማረጋገጫው ለእርስዎ የሚመጥን ነው።
እንግሊዝኛ ቋንቋ በማስተማሩ ሥራ ተጨማሪ ብቃት ለማግኘት እንደ CELTA ወይም Delta የመሳሰሉትን ትምህርቶች መማር የሚፈልጉ ከሆነ TKT ጥሩ መሠረት ይሆንልዎታል።
ይህንን ፈተና ለመፈተን የተለየ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እንዲኖርዎት አይጠበቅብዎትም።
ፈተናው ምን ምን ክፍሎች አሉት?
ማንኛውንም የ TKT ክፍል በጥምረት ወይም በተናጠል ለመፈተን መምረጥ ይችላሉ።
መሠረታዊ ክፍሎች ከ 1-3
- TKT ክፍል 1፦ ቋንቋ የማስተማር ልምድ
- TKT ክፍል 2፦ ቋንቋ ለማስተማር እቅድ ማውጣት
- TKT ክፍል 3፦ የመማሪያ ክፍል አደረጃጀት
የሙያ ስልጠና ክፍሎች
- TKT ኖውሌጅ አባውት ላንጉዌጅ (KL)
- TKT ኮንቴንት ኤንድ ላንጉዌጅ ኢንተግሬትድ ለርኒንግ (CLIL)
- TKT ያንግ ለርነርስ (YL)
ካምብሪጅ ኢንግሊሽ ፈተናን በኢትዮጵያ መፈተን
በኢትዮጵያ TKT ለመፈተን እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ የሚጠቁም መረጃ ይመልከቱ።
በኢትዮጵያ መቼ እና የት ቦታ TKT መፈተን እንደሚችሉ እንዲሁም ለእያንዳንዱ የፈተና ክፍል ምን ያህል እንደሚከፈል ለማወቅ መረጃዎችን ይመልከቱ።
እያንዳንዱ የፈተና ክፍል 80 ጥያቄዎች ሲኖሩት የሚሰጠው ጊዜ 80 ደቂቃ ነው። በፈተና ቀንምን ይጠበቃልየሚለውን ለማወቅ መረጃዎች ይመልከቱ።
ፈተናውን ከተፈተኑ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የፈተናዎትንውጤቶችማግኘት ይችላሉ። ማለፍ ወይም መውደቅ የሚባል ነገር የለም፤ ያገኙት ነጥብ በደረጃዎች ይገለፃል። ደረጃ 1 የሚባለው የመጨረሻው ዝቅተኛ ነጥብ ሲሆን በመስኩ ያለዎት እውቀት እና ችሎታ ውስን እንደሆነ ያሳያል፤ ደረጃ 4 ደግሞ ትልቁ ነጥብ ሲሆን ከፍተኛ እውቀትና ችሎታ እንዳለዎት የሚገለፅበት ነው።