ውጤቶቼን መቼ ነው የማገኘው?
ለ IELTS ፈተና ውጤቶችዎ ረጅም ጊዜ መጠበቅ አያስፈልግዎትም።
ውጤቶችዎን አስቀድመው ለማየት ወደ ተፈታኝ መግቢያ በመለያዎ መግባት ይችላሉ። የIELTS ውጤቶች ለ 28 ቀናት በተፈታኝ ፖርታል ድረ ገጽ ላይ ይቆያሉ ነገር ግን የአፈፃፀምዎ ኦፊሴላዊ ማረጋገጫ ተደርገው ጥቅም ላይ መዋል የለባቸውም። ያስታውሱ፤ IELTS ለUKVI የሚወስዱ ከሆነ ውጤትዎን በተፈታኝ ፖርታል ድረ ገጽ ላይ ማየት አይችሉም።
ከፈተናው ዕለት ከ 13 የቀን መቁጠሪያ ቀናት በኋላ ውጤቶችዎን አስቀድመው ማየት ይችላሉ።
የውጤቴን አካላዊ ቅጂ መቼ እገኛለሁ?
በወረቀት የሚሰጥ ፈተና ከተጠናቀቀ ከ 13 ቀናት በኋላ የ IELTS ፈተናዎን ነጥብ የወረቀት ግልባጭ (የፈተና ሪፖርት ቅጽ (Test Report Form)) የፈተና ማዕከላችን ድረስ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ ወይም በተጻፈ ደብዳቤ የወከሉትን ሰው በመላክ መቀበል ይችላሉ።
የ IELTS ውጤቶች በስልክ ወይም በኢሜል አይገለጹም።
የፈተና ውጤት መረጃዎን ከጣሉ ለፈተና ማዕከሉ ያሳውቁ።
ለሚያመለክቱባቸው ተቋማት በቀጥታ የፈተና ሪፖርት ቅጽዎን (TRF) እንልካለን
ተቋማት የፈተና ሪፖርት ቅጽዎን ኦርጂናል ኮፒ ይፈልጋሉ። የውጤትዎ ፎቶ ኮፒ ተቀባይነት አይኖረውም።
እስከ አምስት ተጨማሪ የ TRF ቅጂዎች በቀጥታ ለሚያመለክቱባቸው ተቋማት (ለምሳሌ፡ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የኢሚግሬሽን ጽ/ቤቶች፣ ወዘተ) መላክ እንችላለን። ይህንን እንድናደርግ የሚፈልጉ ከሆኑ፣ ለፈተናዎ ቦታ ሲይዙ ተገቢውን አድራሻ ያካትቱ።
የተቋሙን ሙሉ የፖስታ አድራሻ መስጠትዎን አይዘንጉ። ያለ ሙሉ አድራሻ ተቋሙ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ካስገባናቸው በኋላ ውጤቶቻቸውን ለማየት የሚያስችለውን የ IELTS ፈተና ሪፖርት ማረጋገጫ ቅጽ ማግኘቱን ማረጋገጥ አንችልም። ምናልባት ይህን አገልግሎት ማግኘት የማይችሉ ከሆነ፣ የእርስዎን TRF በፖስታ እንልካለን።
የ IELTS ውጤቶቼን ተጨማሪ ቅጂዎች ማግኘት እችላለሁ?
እኛ ካቀረብናቸው አምስት ኮፒዎች በተጨማሪ የእርስዎን የፈተና ሪፖርት ቅጽ ሌላ ቅጂ ለሚታወቅ ድርጅት እንድንልክልዎት ከፈለጉ፣ ወደ አለምአቀፍ መዳረሻዎች በፖስታ ለመላክ በቅጂ 200 ብር የአስተዳደር ክፍያ መክፈል አለብዎት።
የፈተና ማዕከልዎ ዝግ ከሆነ፣ ከ ielts.org ድረ ገጽ ተጨማሪ የፈተና ሪፖርት ቅጾችን ማዘዝ ይችላሉ። (https://www.ielts.org/book-a-test/additional-trf-form)
የተቋሙን አድራሻ ማቅረብ እና "ለተጨማሪ የፈተና ሪፖርት ቅጽ ማመልከቻ" መሙላት ይኖርብዎታል። ከዚያም የፈተና ሪፖርት ቅጽዎን በቀጥታ ወደ ተቋሙ እንልካለን።
ተጨማሪ የፈተና ሪፖርት መጠየቂያ ለመፈጸም 3 ቀናት ያህል ሊወስድ እንደሚችል ልብ ይበሉ።
የ IELTS ነጥቤ ምን ማለት ነው?
ለእያንዳንዱ የፈተና ክፍል የ IELTS ከ 0-9 ያሉ የባንድ ነጥቦች ይሰጡዎታል፣ ይህም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎን ያንፀባርቃል።
የእርስዎ የፈተና ሪፖርት ቅጽ ለእያንዳንዱ አራት ክህሎቶች (ማዳመጥ፣ ማንበብ፣ መጻፍ እና መናገር) አንድ ነጥብ እና አጠቃላይ የባንድ ነጥብን ያሳያል። በእያንዳንዱ የፈተና ክፍል ሙሉ የሆኑ የባንድ ነጥቦችን (ለምሳሌ 5.0፣ 6.0፣ 7.0) ወይም ግማሽ የባንድ ውጤቶችን (ለምሳሌ 5.5፣ 6.5፣ 7.5) ሊያገኙ ይችላሉ።
ውጤትዎ ምን ማለት እንደሆነ ተጨማሪ እዚህ ይወቁ
የ IELTS ውጤቶቼ ዋጋ የሚኖራቸው ለምን ያህል ጊዜ ነው?
ፈተናውን ከወሰዱ ጀምሮ የእንግሊዘኛ ቋንቋዎን ለመጠበቅ ወይም ለማሻሻል ጥረት እንዳደረጉ ማስረጃ ካላቀረቡ በስተቀር ድርጅቶች ብዙውን ጊዜ ከሁለት ዓመት በላይ የሆናቸው ውጤቶችን አይቀበሉም። የ IELTS አጋሮች ከሁለት ዓመት በላይ የሆናቸው የፈተና ውጤቶችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አይችሉም።
IELTS በኮምፒውተር፣ IELTS በወረቀት፣ እና IELTS ለ UKVI በኮምፒውተር፡
በውጤትዎ ዙሪያ ጥያቄ ካልዎት የ Enquiry on Results Online ቅፅ በተፈታኝ ፖርታል ላይ የሚያገኙ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ በመፈፀም መስተናገድ ይችላሉ።
የ IELTS ፈተናዬ እንደገና እንዲታረም ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?
እርስዎ የጠበቁትን ውጤት ካልተቀበሉ፣ ፈተናዎ እንደገና እንዲታረም ማመልከት ይችላሉ። ይህም በውጤቶች ላይ ምርመራ (Enquiry On Results) ይባላል። እንደገና እንዲታረሙ የሚፈልጓቸው የትኞቹን የፈተና ክፍሎች እንደሆነ መምረጥ የሚችሉ ሲሆን ይህንን ለፈተናው በተቀመጡበት የፈተና ማዕከል መጠየቅ ይኖርብዎታል።
የዚህ አገልግሎት ክፍያ ዋጋው 95 ፓውንድ ሲሆን፣ የእርሶ ነጥብ በየትኛውም የፈተና ክፍል ላይ ከጨመረ ገንዘቡ ተመላሽ ይደረጋል።
በድጋሚ እንዲታረም ለመጠየቅ ፈተና ከተወሰደበት ቀን ጀምሮ ከስድስት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ማመልከት ያስፈልግዎታል።
ከዚህ በታች ካለው የማውረጃ ክፍል በውጤቶች ላይ ምርመራ መጠየቂያ ቅጽን ያውርዱ (ቅጽ ያክሉ) እና ለፈተናው በተቀመጡበት የፈተና ማዕከል ያስገቡ። የእርስዎን የፈተና ውጤት መግለጫ ቅጽ እና የክፍያ ማረጋገጫን ማያያዝዎን ያረጋግጡ።
በውጤቶቹ ላይ የሚቀርቡ የምርመራ ጥያቄዎች ለመጠናቀቅ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ይወስዳሉ።
የ IELTS ፈተናዬን በድጋሚ መውሰድ እችላለሁ?
የ IELTS ፈተናን በድጋሚ መወሰድ ላይ ምንም አይነት ገደቦች የሉም። እርስዎ ዝግጁ እንደሆኑ እንደተሰማዎት ወዲያውኑ ለፈተና ቦታ መያዝ ይችላሉ።
ፈተናውን እንደገና ከመውሰድዎ በፊት እንግሊዝኛዎን ለማሻሻል ጉልህ ጥረት ካላደረጉ ውጤቱ የማይጨምር መሆኑን ልብ ይበሉ። የልምምድ ፈተና ለመውሰድ እና ደረጃዎን ለመገምገም የዝግጅት ክፍሉን ይጎብኙ።