ስለ የ IELTS ፈተና ቀንዎ መረጃ እና ምክር
ስለ የ IELTS ፈተና ቀንዎ ትንሽ የመጨነቅ ስሜት ሊሰማዎ ይችል ይሆናል። ነገሮች በተቻለ መጠን ያለምንም እንከን ይጠናቀቁ ዘንድ፣ በፈተናዎ ቀን ምን እንደሚሆን እንዲረዱ ለማገዝ አንዳንድ መረጃዎችን አዘጋጅተናል።
ለ IELTS ፈተናዎ ጥሩ ጊዜ ላይ መድረስ ይኖርብዎታል። ከፈተናው በፊት ቢያንስ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ ፈተናዎ ምን ሰዓት ላይ እንደሚጀምር ያውቁ ዘንድ ኢሜል ይደርሰዎታል። እንዲሁም ኢይሜሉ በፈተናው ቀን ስላሉ የአሰራር ሂደቶች እና የጊዜ ሰሌዳዎች መረጃን ይሰጥዎታል። ዘግይተው ከደረሱ፣ ፈተናውን እንዲወስዱ ላይፈቀድሎት ይችላል።
በአካለ ስንኩልነት ወይም በሌላ ሁኔታ ምክንያት ልዩ ዝግጅቶችን ጠይቀው ከነበረ፣ በፈተናው ቀን ላይ ማስተካከያዎች ይደረጉልዎታል። እባክዎን ስድስት ሳምንታት አስቀድመው በፈተና ማዕከሉ ያሉ ሰራተኞቻችንን ያግኙ።
ዝግጁ መሆንዎን እና አስቀድመው የሚበላ እና የሚጠጣ ነገር እንዳለዎት ያረጋግጡ። ወደ ፈተና ክፍሉ ውስጥ ምግብ እንዲያስገቡ አይፈቀድም እና ውሃን ውስጡን በሚያሳይ ጠርሙስ እንዲያስገቡ ብቻ ይፈቀድልዎታል።
አንዳንድ የIELTS የፈተና ማዕከሎቻችን የIELTS የንግግር ፈተናን በቪዲዮ ጥሪ እያቀረቡ ነው። ይህ ማለት የIELTS የንግግር ፈተናን የበለጠ ተደራሽነትንና እና ተገኝነትን ይጨምራል። የIELTS በቪዲዮ ጥሪ የሚሰጥ የንግግር ፈተና ከገጽ ለገጽ ፈተናው እኩል ከፍተኛ ጥራት ያለው የማንነት ማረጋገጫ ደረጃ አለው፡፡በተጨማሪም ፈተናው በይዘት፣ በውጤት አሰጣጥ፣ በጊዜ፣ በጥያቄ ቅርፀት እና በደህንነት በኩል በአካል ከሚከናወነው የንግግር ፈተና ጋር ተመሳሳይ ነው። በIELTS Talk ፈታኝ የሚቀርበው የቪዲዮ ጥሪ የንግግር ፈተና ፣ በአካል ወይም ገጽ ለገጽ የሚሰጠውን የንግግር ፈተና ባሀሪያቶቸ የጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን የአካባቢዎን የብሪቲሸ ካወንሰለ ፈተና ማእከል ያግኙ፡፡