ያስታውሱ ይህ IELTS ለAcadmic እና General Training መመሪያ ነው IELTS ለUKVI በሚመለከት በዚህ ገጽ ላይ ያንብቡ::
የ IELTS ፈተናዎን መሰረዝ
የፈተናው ቀን ከመድረሱ እስከ አምስት ሳምንታት አስቀድሞ የIELTS ፈተናዎን ከሰረዙ፣ ከፈተናው ክፍያ ገንዘብ ላይ 25 ከመቶ ለአስተዳደር ክፍያ ተቀንሶ ተመላሽ ገንዘብ ይቀበላሉ። ለUKVI ደግሞ ከፈተናው ክፍያ ገንዘብ ላይ የአስተዳደር ክፍያ 50 ከመቶ ይቀነሳል፡፡
ተመላሽ ገንዘቦችን ለመፈጸም ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ልብ ይበሉ።
IELTS ፈተናው አምስት ሳምንታት ከቀረው በሁዋላ ግን የከፈሉበትን ገንዘብ ተመላሽ የማይሆን እንደሆነ ማሳወቅ ስንወድ በዚሀ ፖሊሲ የማይካተቱት
- ከባድ ሕመም ወይም ሕክምና ( ምሳሌ፡ ሆስፒታል መግባት ወይም ከባድ ጉዳት)
- ሐዘን - የቅርብ የቤተሰብ አባል ማጣት
- ችግር ወይም አሰቃቂ ክስተት (ለምሳሌ የወንጀል ሰለባ መሆን ወይም በትራፊክ አደጋ ውስጥ መሳተፍ)
- ወታደራዊ አገልግሎት ምክንያት ከሆኑ ብቻ ነው፡፡
የፈተና ቀንዎን ለመሰረዝ (ለአካዳሚክ /Academic እና ጠቅላላ/General) ወደ ተፈታኝ ፖርታል በመግባት የስረዛ ጥያቄ በማቅረብ አስፈላጊ ሰነዶችን ይጫኑ።
በፈተናው ቀን ላይ ሕመምን እንደነበር የሚያረጋግጥ ኦርጅናል የሕክምና ማስረጃ ፈተና ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ከተመላሽ ገንዘብ መጠየቂያ ወይም የፈተና ቀን ማስተላለፊያ ቅፅ ጋር ተያይዞ ከቀረበ፣ ከፈተና ክፍያው ላይ 25 ከመቶ የአስተዳደር ክፍያ ተቀናሽ (ለUKVI ደግሞ 50 ከመቶ ተቀናሽ) ሆኖ ቀሪው ተመላሽ ይደረጋል።
በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ የሚቀርቡ ኦርጅናል የሕክምና ማስረጃዎች ብቻ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። ከፈተናው በኋላ ባለው አምስተኛ የስራ ቀን በአዲስ አበባ ባለው ቢሯችን ሁለቱም አስፈላጊ ሰነዶች የማይደርሱን ከሆነ፣ እንደ ቀሪ ይመዘገቡ እና ሁሉም የይገባኛል ጥያቄዎችዎ ውድቅ ይደረጋሉ።
በፋክስ ወይም በኢሜይል የሚላኩ ኮፒዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። የሕክምና ማስረጃዎችን በአካል በመምጣት ማቅረብን እንመክራለን።
በቤተሰብ አባላት የተጻፉ የሕመም ማስታወሻዎችን እንደማንቀበል ልብ ይበሉ።
የፈተና ቀን እንዲተላለፍ መጠየቅ
የፈተና ቀንዎን መጀመሪያ ካስያዙት ቀን መለወጥ ካስፈለገዎት፣ የፈተና ቀንዎ ከመድረሱ እስከ አምስት ሳምንታት አስቀድመው ድረስ፣ ያለክፍያ የፈተና ቀን እንዲተላለፍ መጠየቅ ይችላሉ።
አዲሱ የፈተና ቀን ከመጀመሪያው ቀን በሶስት ወራት ውስጥ መሆን እንዳለበት ልብ ይበሉ። ሕመም በሚያጋጥምበት ጊዜ፣ ኦርጅናል የሕክምና ማስረጃ ፈተና ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ከተመላሽ ገንዘብ መጠየቂያ ወይም የፈተና ቀን ማስተላለፊያ ቅፅ ጋር ተያይዞ ከቀረበ፣ በፈተናው አምስት ሳምንታት ውስጥ ማስተላለፍ የሚቻል ይሆናል።
አዲስ ተለዋጭ የፈተና ቀን ከተያዘልዎ (ከፈተናው አስቀድሞ ወይም በሕመም ምክንያት) እና በሁለተኛው የፈተና ቀን የታመሙ ከሆነ፣ ለፈተና ክፍያ ተመላሽ ገንዘብም ሆነ በተጨማሪ ወደ አዲስ የፈተና ቀን ማስተላለፍ መብት የለዎትም።