በኢትዮጵያ ውስጥ የIELTS ፈተናን የት መውሰድ እችላለሁ?

በኢትዮጵያ ውስጥ በአዲስ አበባ እና ጎንደር  በሚገኙ 2 ሕጋዊ የፈተና ማዕከላት ሁለት ምቹ የIELTS ፈተና ቀናትን እናቀርባለን። ፈተናውን በወረቀት ላይ ወይም በኮምፒውተር በመታገዝ መውሰድ ይችላሉ። ፈተናውን በሚመርጡት መንገድ በማዕከሎቻችን ይውሰዱ።

IELTS በወረቀት የሚሰጥባቸው ቦታዎች 

አዲስ አበባ፣ ጎንደር

IELTS በኮምፒውተር የሚሰጥባቸው ቦታዎች

አዲስ አበባ

 

ዋጋው ምን ያካተተ ነው?

የIELTS ዋጋችን የተመረጡ ጠቃሚ ፈተና መዘጋጃ ስልጠናዎችን፣ ነጻ የመለማመጃ ፈተናዎችንና ሌሎች ግብዓቶችን ያካተተ ነው።  

የሰዓት ፕሮግራም

የማዳመጥ ማንበብ እና መጻፍ ፈተናዎች ያለምንም እረፍት በተከታታይ የሚሰጡ ይሆናል። በኮቪድ ወረርሽኝ ምክን ያት ፈተናዎችን ጠዋትና ከሰዓት በማካሄድ ላይ ነን። ሁሉም ፈተናዎችን ርቀትን ጠብቀው ይከናወናሉ። 

IELTS በወረቀት ላይ የሚወስዱ ከሆነ የንግግር ፈተናዎ ሌሎች ፈተናዎችን ከወሰዱበት ቀን እስከ ሰባት ቀናት ቀደም ብሎ ወይም በሚቀጥሉት ሰባት ቀናት ውስጥ ይደረጋል። ከ48 ሰዓታት በፊት የንግግር ፈተናዎን ሰዓት የሚገልጽ ኢሜይል ይደርስዎታል።

የንግግር ፈተና ሰዓት አመራረጥ 

IELTS በወረቀት ወይም በኮምፒውተር ለመውሰድ ሲመዘገቡ የንግግር ፈተና ሰዓትዎን መምረጥ ይችላሉ። በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንት የፈተናዎን ሰዓት መቀየር ካለብን በኢሜይል እናሳውቅዎታለን።

በዩናይትድ ኪንግደም መስራት፣ መኖር ወይም መማር ይፈልጋሉ?

ለስራ ወይም ለትምህርት በሚጓዙበት ጊዜ ቪዛ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፣ ለቪዛ እና የውጪ ሃገር ጉዞ የተዘጋጀውን ልዩ IELTS UKVI አንዳንድ ጊዜ መውሰድ ይኖርብዎታል።