የ IELTS ፈተናን በብሪቲሽ ካውንስል ይውሰዱ እና የሚያስፈልግዎትን እርዳታ ያግኙ።
ለ IELTS ፈተናዎ ቦታ ሲይዙ፣ ወደሚፈልጉበት ለመድረስ የሚያስፈልገውን ውጤት በማምጣት ላይ ማተኮር ይኖርብዎታል።
ለዚህ ነው ለ IELTS በብሪትሽ ካውንስል ለመፈተን ሲዘጋጁ፣ የቦታ መያዝ ሂደቱ በተቻለ መጠን ቀላል መሆኑን በማረጋገጥ፣ እስከ ፈተናው ቀን ድረስ የሚያስፈልግዎትን ድጋፍ የምናቀርበው።
ለ IELTS በብሪትሽ ካውንስል ቦታ ሲይዙ ልዩ የዝግጅት ቁሳቁሶች እና ተጨማሪ ጥቅሞችን ያግኙ
- ነፃ ያልተወሰነ የ Road to IELTS Last Minute ኮርስ ተደራሽነት፡ ይህም ምክር እና የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ዘጠኝ ቪዲዮዎችን፣ 100 መስተጋብራዊ ተግባሮችን እና ለአራቱም ክህሎቶች እያንዳንዳቸው ሁለት የልምምድ ፈተናዎች — እና በተጨማሪም ለ IELTS በብሪትሽ ካውንስል ቦታ ሲይዙ ነጻ ነው።
- ከክፍያ ነጻ የልምምድ ፈተናዎች፡ ነጻ የልምምድ ፈተናዎችን በመስመር ላይ በ takeielts.org/prepare ወይም ለ IELTS Academic እና General Training የናሙና ፈተናዎችን የያዘውን የ IELTS የልምምድ መጽሐፍ ቅጂን ይዘዙ።
- በጉዞ ላይ እያሉ ይዘጋጁ፡ በእንቅስቃሴ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ እንኳን የእንግሊዝኛ ችሎታ ለማሻሻል ሊረዱ የሚችሉ በርካታ የነፃ ፈጠራ መተግበሪያዎች አሉን።
- የባለሙያ ድጋፍ፡ ከቪዲዮዎች እና መፅሐፎች እስከ በመረጃ መረብ የሚሰጡ ኮርሶች፣ ፈተናዎን በደንብ እንዲሰሩ የሚያግዙዎ ምርጥ የዝግጅት ቁሳቁሶችን ማግኘት ይችላሉ።
- ቀላል ቦታ አያያዝ፡ በመረጃ መረብ / በድረ ገጽ ላይ ወይም በኦፊሴላዊ የብሪትሽ ካውንስል የIELTS ፈተና ማዕከል በመምጣት ቦታ መያዝ ይችላሉ።
- አመቺ ቀኖች እና ቦታዎች፡ በ ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት የፈተና ቦታዎች አሉን። ይህ ማለት ፈተናዎችዎን የት እና መቼ መውሰድ እንደሚፈልጉ በርካታ አማራጮች አሉዎት ማለት ነው።
- አምስት ተጨማሪ የፈተና ሪፖርት ቅጾች (TRF) በነፃ፡ ለሚያመለክቱባቸው ተቋማት (ለምሳሌ፡ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የኢሚግሬሽን ጽ/ቤት ወዘተ) በቀጥታ የሚላኩ አምስት ተጨማሪ የፈተና ሪፖርት ቅጂዎችን ይስጡ።
- በጥንቃቄ የተመረጡ ቦታዎች፡ ሁሉም 850 ኦፊሴላዊ የብሪትሽ ካውንስል የ IELTS ፈተና ማዕከሎች የሚጠብቋቸው አይነት ዘመናዊ ተቋማት እና በጣም ጥሩ ቦታ ያላቸው ያገኛሉ።
- ደንበኛ ተኮር የሆኑ ሰራተኞች: የፈተና ቀንዎ ያለ ችግር ማለፉን ለማረጋገጥ የሚተጉ የሰለጠኑ እና ልምድ ያላቸው ሰራተኞች።
- ተስማሚ የመክፈያ አማራጮች፡ የፈተናውን ክፍያ በየትኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በቀላሉ በቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታችን ገቢ ማድረግ ይችላሉ። ወይም በየትኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለብሪቲሽ ካውንስል ገቢ ማድረግ ይችላሉ።