ሪቲሽ ካውንስል በኢትዮጵያ IELTS Acadamic እና General Training፣ IELTS ለ UKVI ፈተናዎችን ይሰጣል

ፈተናውን ከኛ ጋር ሲወስዱ ዕወቅና ካለው ማዕከል መውሰድዎን እርግጠኛ መሆን ይችላሉ

የምንሰጣቸው ፈተናዎች

Test type Fee (ETB) Book
IELTS Academic ወይም General Training - paper-based test 9,775
Book now 
IELTS Academic ወይም  General Training - computer-delivered test 9,775
Book now 
IELTS for UKVI (Academic ወይም General Training) 10,835 Book now 
IELTS Life Skills (A1 ወይም B1) 7,950 Book now 

*ለIELTS Academic ወይም General Training ፈተና ክፍያ ከሚያዝያ 1 ጀምሮ 171 ፓውንድ ነው 

**IELTS ለUKVI ፈተና ክፍያ ከሚያዝያ 1 ጀምሮ 191 ፓውንድ ነው 

ለፈተናዎ ቦታ ከመያዝዎ በፊት

  1. በእጅዎ ትክክለኛ መታወቂያ (ፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ) እንዳለዎት እርግጠኛ ይሁኑ፣ ይህም ለፈተናዎ ቦታ በሚይዙበት ጊዜ ግልጽ የሆነ የመታወቂያ ፎቶኮፒ ገቢ ማድረግ ስለሚያስፈልግዎት ነው። ከ18 ዓመት እድሜ በታች ያሉ እጩዎች ለፈተና ቦታ ለማመልከት እንዲችሉ ከወላጅ ወይም አሳዳጊ የጽሁፍ ፈቃድ ማቅረብ እንዳለባቸው ልብ ይበሉ።
  2. ስለ ፈተናው ቅርፅ፣ የጥያቄ ዓይነቶች እና የፈተናው ውጤቶች አስፈላጊ መረጃ የያዘ የእጩዎች መረጃችንን ያውርዱ እና ያንብቡ። IELTS ከ 16 ዓመት በታች ለሆኑ ተፈታኞች እንደማይመከር ልብ ይበሉ። 
  3. የፈተናውን ክፍያ በየትኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በቀላሉ በቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታችን ገቢ ማድረግ ይችላሉ (የክፍያ አፈጻጸም መመሪያ እዚህ ያግኙ)።  ወይም በየትኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለብሪቲሽ ካውንስል ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
  4. ክፍያውን ከፈፀሙ በኋላ እባክዎ የሚከተሉትን ሰነዶች በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያስረክቡን፦
  • በኢንተርኔት መመዝገብዎን የሚያረጋግጥ የኢሜይል ኮፒ፣
  • ጊዜ ያላለፈበት የመታወቂያዎን (ፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ) ኮፒ እና ዋናውን፣
  • ለፈተናው ክፍያ የፈፀሙበትን ሲፒኦ፣ 

ከላይ የተጠቀሱት ሰነዶች በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ካልደረሱን የሞሉት ማመልከቻ ወዲያውኑ ውድቅ ይደረጋል።

የ IELTS ፈተና ቀን ማረጋገጫ

የቦታ መያዝ ሂደቱን ካጠናቀቁ በኋላ፣ ፈተናዎ የሚጀምርበትን ጊዜና የሚሰጥበትን ቦታ አድራሻ የሚገልጽ ማረጋገጫ ይደርስዎታል። 

የንግግር ፈተናዎ እንደ ሌሎቹ ክፍሎች በተመሳሳይ ቀን ወይም ከዋና ፈተናዎ በፊት ወይም በኋላ በ 7 ቀን ጊዜ ውስጥ በሌላ ቀን ሊደረግ ይችላል። የፈተናው ማዕከል ለንግግር ፈተናው ቀን ማረጋገጫ ይልክልዎታል።

ለፈተናዎ ቦታ ከያዙ በኋላ፣ ነፃ ኦንላይን ኮርስ የሚያገኙበትን የሚስጥር ኮድ የያዘ ኢሜይልም ይደርስዎታል፡ Road to IELTS

የተፈታኝ ፖርታልን ለማግኘት የሚጠቀሙበትን የ IELTS መለያ ቁጥርዎንም ይቀበላሉ።  እባክዎን ለፈተናዎ ቦታ ሲይዙ የኢሜይል አድራሻዎን በትክክል ማካተትዎን ያረጋግጡ።

በዚህ ክፍል