ለፈተናው በሚመዘገቡበት ጊዜ የIELTS ደንቦች እና ሁኔታዎችን ማንበብ እና መቀበልዎ አስፈላጊ ነው።

ደንቦቹ እና ሁኔታዎቹን በማመልከቻ ቅጹ ውስጥ በተካተተው፣ የዕጩ ተፈታኞች የመረጃ በራሪ ወረቀት ውስጥም ያገኟቸዋል። 

ደንቦቹ እና ሁኔታዎቹ የሚከተሉትን ዝርዝሮች ጨምሮ አስፈላጊ መረጃዎችን ያካትታሉ፡

  • ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች
  • ለፈተናዎ ሲቀመጡ የሚወሰዱ የደህንነት ጥንቃቄዎች
  • የውጤቶች ሂደት
  • የስረዛ ሂደት
  • መረጃዎን እንዴት እንደምንጠቀምበት።

በድረ ገጽ ለIELTS  ሲመዘገቡ በደንቦች እና ሁኔታዎች ሳጥን ላይ ምልክት ሲያደርጉ፣ የ IELTS ደንቦች እና ሁኔታዎች እንዳነበቡ እና እንደተረዱ እንዲሁም እነሱን ለማክበር መስማማትዎን እያረጋገጡ ነው።