የእይታ፣ የመስማት፣ የመናገር ወይም የመማር ችግሮች ካለብዎ የIELTS የፈተና ማዕከላችን ሊረዳዎት ይችላል። እንደ ልዩ ፍላጎትዎ የተሻሻለ የIELTS ፈተና የሚፈልጉ ከሆነ፣ ለፈተና ማዕከሉ የሶስት ወራት ማሳሰቢያ ይስጡ።  

ልዩ ዝግጅቶች (ለምሳሌ፣ ተጨማሪ ጊዜ) መደረግ ካለባቸው ለፈተና ማዕከሉ ከስድስት ሳምንታት በፊት ማሳሰቢያ ይስጡ።

የአካል ጉዳት ወይም የትኛውም አይነት ልዩ ፍላጎቶች ሊኖሩዎት ቢችልም እንኳን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎ ያለ አድልዎ ይገመገማል።

ልዩ ዝግጅቶች ምንን ያካትታሉ?

  • የብሬይል ወረቀቶች
  • አስፈላጊ መዝጊያዎች እና መቆሚያዎች ያሉት ለየት ያለ የማዳመጫ ሲዲ
  • ለማዳመጥ ፈተናው የከንፈር-ንባብ ስሪት
  • ትልቁ ሕትመት ወይም በብሬይል ያሉ የንግግር ተግባር ካርዶች።

ምን ዓይነት እርዳታ ማግኘት እችላለሁ?

የማየት ዕክል ካለብዎት፣ የሚከተሉን ማቅረብ እንችላለን፡

  • ትልልቅ ሕትመት
  • የብሬይል የፈተና ወረቀቶች
  • ለእርስዎ መልሶች የሚጽፍ አንድ የቃል ፀኃፊ።

የመስማት ችግር ካለብዎ፣ የሚከተሉትን ልንሰጥ እንችላለን፡

  • ልዩ የማጉያ መሳሪያዎች
  • የማዳመጥ ሞጁሉን የከንፈር-ንባብ ስሪት

ዲስሌክሲያ ካለብዎ፣ የሚከተለውን ማዘጋጀት እንችላለን፡

  • ለማንበብ እና ለመፃፍ ፈተናዎች ተጨማሪ ጊዜን።

የተሻሻለ የIELTS የፈተና ስሪት ሊፈልጉ የሚችሉ ልዩ ፍላጎቶች ካሉዎት እባክዎን የፈተና ማዕከላችንን ያነጋግሩ።