በሚፈተኑበት ቀን ትክክለኛዎቹን ቅፆች እና መሣሪያዎች በሙሉ ይዘው መምጣትዎት ምንም አይነት ጭንቀት እንዳይሰማዎት እና ከፈተናው እንዳይዘገዩ ይረዳዎታል።

ከቤት ከመውጣትዎት በፊት፦

 • በትምህርት ቤትዎ በኩል የሚፈተኑ ተማሪ ከሆኑ ዩኒፎርም ይልበሱ።
 • ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መድረስዎት ዘና ለማለት ይረዳዎታል።
 • የመንገድ መጨናነቅ ወይም የጉዞ መስተጓጎል ቢያጋጥምዎት እንዳይዘገዩ ከቤት ቀደም ብለው ይውጡ (እንዲሁም አማራጭ የጉዞ እቅድ በአእምሮዎት ያስቡ)።

መፈተኛ ክፍል ውስጥ ይዘው መግባት ያሉብዎት ነገሮች፦

 • መታወቂያዎትን
 • የመፈተኛ ፈቃድ
 • በግልፅ በሚያሳይ መያዣ ውስጥ የተቀመጠ እስክሪብቶ እና እርሳስ
 • ሂሳብ ማስሊያ (የፈተና ቦርድዎት የሚፈቅደውን አይነት)
 • ለሚወስዱት የፈተና አይነት የሚያስፈልጉ ተጨማሪ መሣሪያዎች።

ያስታውሱ፦

 • ተንቀሳቃሽ ስልክም ይሁን ማንኛውንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ይዞ መግባት አይፈቀድም።
 • ውድ ንብረቶችዎን ይዘው አይምጡ።

ለተግባር፣ ለቃል፣ በኮምፒውተር ለሚሰጥ እና ለሥነ ጥበብ/ለንድፍ ፈተናዎች ከላይ ከተገለፁት የተለዩ ደንቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ እባክዎ ያስታውሱ።

ለፈተና የሚጠቅሙ ተጨማሪ ሃሳቦችን እና ድጋፎችን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ። 

ልዩ ዝግጅቶች ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።

የፈተና ፕሮግራሞችን እዚህ ይመልከቱ። 

መታወቂያ እና የመፈተኛ ፈቃድ

ሁሉንም ፈተናዎች ሲፈተኑ መታወቂያዎትን እና የመፈተኛ ፈቃድዎትን ይዘው መምጣት አለብዎት።

ተቀባይነት ያላቸው የትኞቹ መታወቂያዎች ናቸው?

ተቀባይነት ያላቸው መታወቂያዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ብቻ ናቸው፦

 • ፓስፖርት
 • የቀበሌ መታወቂያ

ከሁለቱ አንዱ እንኳን ከሌለዎት እባክዎ ከመፈተኛ ቀንዎት ብዙ ጊዜ አስቀድመው አስተማሪዎትን ወይም የብሪቲሽ ካውንስልን ተወካይ ያነጋግሩ።

የመፈተኛ ፈቃድ ምንድን ነው?

የመፈተኛ ፈቃድ የሚባለው ለፈተና መመዝገብዎትን የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው። ፈቃዱ ላይ የመረጧቸው የፈተና አይነቶች ዝርዝር፣ የእያንዳንዱ ፈተና መፈተኛ ቀናት፣ ስምዎት፣ የተወለዱበት ቀን እና የትምህርት ቤትዎ ስም ይፃፋል። 

በትምህርት ቤት በኩል የሚፈተኑ ተማሪ ከሆኑ ከፈተናው ጊዜ አስቀድመው የመፈተኛ ፈቃድዎትን ከትምህርት ቤትዎ መቀበል ይገባዎታል። የግል ተፈታኝ ከሆኑ ከፈተናው ቀን ወደ ሶስት ሳምንታት ከሚጠጋ ጊዜ አስቀድመው የመፈተኛ ፈቃድዎትን በፖስታ ቤት በኩል ማግኘት ይገባዎታል።