በኮቪድ-19 የተነሳ በብዙ ሃገራት በአካል የሚካሄደው የIELTS ፈተና በመቋረጡ ምክንያት IELTS Indicator የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትዎን ለማረጋገጥ የሚሆን በኢንተርኔት ላይ የሚሰጥ ፈተና ነው።

ስለ IELTS Indicator

  ይህ ሙሉ ዕውቅና ያለው የIELTS  ምርት ሲሆን አራቱን መሰረታዊ ክህሎቶች ይመዝናል
 • ማዳመጥ 
 • ማንበብ 
 • መጻፍ
 • መናገር 

ውጤትዎ በሰባት ቀናት ውስጥ ይደርስዎታል – የውጤትዎ ሪፖርት በእያንዳንዱ ክህሎት ላይ አመላክች ውጤት እና አጠቃላይ የተጣራ አመላካች ውጤት የያዘ ነው. ያስታውሱ IELTS Indicator በአካል ለሚሰጠው የIELTS ፈተና ምትክ ሊሆን አይችልም.

የIELTS Indicator ዋና ዋና ጥቅሞች 

ደህንነት

በኢንተርኔት የሚሰጥ ፈተና በመሆኑ በቀላሉ ደህንነትዎ ተጠብቆ ከቤትዎ ሊወስዱት ይችላሉ

ተደራሽነት

ፈተናው በየሳምንቱ በተመረጠ ሰዓት ይሰጣል – you simply log in to our secure browser.

ተዓማኒነት

ይህ ፈተና በIELTS ፈታኞች ስለሚመዘንና ትክክለኛ የIELTS ጥያቄዎችን ያካተተ በመሆኑ የትምህርት ተቋማት ስለተፈታኙ ክህሎት አስተማማኝ ምልክታ እንደሚሰጣቸው ያምናሉ።

ፈተናው እንዴት ይካሄዳል

IELTS Indicator በኢንተርኔት ላይ የሚሰጥ በየሳምንቱ በተወሰነ ሰዓት ይካሄዳል። የማዳመጥ የመጻፍና የማንበብ ፈተናዎችን በተመሳሳይ ጊዜ ይወስዳሉ። የመናገር ክህሎት ፈተና ከሌሎቹ ፈተናዎች ቀድሞ ወይም በፊት መካሄድ ይኖርበታል።

IELTS Indicator በማን ተቀባይነት አለው?

ለፈተና ከመመዝገብዎ በፊት የIELTS Indicator ውጤትን የሚቀበሉ ተቋማትን ዝርዝር እዚህ ይመልከቱ። የመረጡት ዩኒቨርሲቲ በዝርዝሩ ውስጥ ከሌለ ይህን መመዘኛ ፈተና እንደሚቀበሉ በቅድሚያ ያረጋግጡ

IELTS Indicator ለትምህርት አገልግሎት ለሚወሰድ ፈተና የተዘጋጀ ነው ወደ ውጪ ሀገር ለመሄድ የሚያገለግል አይደለም።

ክፍያ 

ታክስን ጨምሮ የELTS Indicator ፈተና ክፍያ የአሜሪካን ዶላር ነው

ለIELTS Indicator ፈተና ከመመዝገብዎ በፊት የሚከተሉትን ዝርዝር ነጥቦች ማወቅ ይኖርብዎታል:

 • ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ የቅድመ ወይም ድህረ ክፍያ ካርዶችን እንቀበላለን
 • የተለያዩ ክፍያ ካርዶችን እንቀበላለን እነዚህም VISA፣ Master Card፣ JCB፣ Diners International፣ Discover፣ American Express፣ Apple Pay እና Google Pay
 • አቅራቢያዎ ካለ ባንክ የተሰጠዎ የቅድመ ክፍያ ካርድ ካለዎት ከፍያዎን ከመፈጸምዎ በፊት ባንክዎን ያነጋግሩ
 • ክፍያዎ እንደ አለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ሊታይ ስለሚችል ስለ ክፍያው በቅድሚያ ያሳውቁ
 • ክፍያው በአሜሪካን ዶላር ሊከፈል ይገባል
 • ክፍያውን ለመፈጸም በቂ ገንዘብ በአካውንትዎ ላይ እንዳለ ማረጋገጥ አለብዎት

ውጫዊ ማያዣዣዎች