IELTS General Training – ተግባራዊ የዕለት ተዕለት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎቶች እንዳለዎት ያረጋግጡ

IELTS General Training የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃትን በተግባራዊ የዕለት ተዕለት አውድ ይለካል። ተግባራቱ እና ፈተናዎቹ የሥራ ቦታ እና የማህበራዊ ሁኔታዎችን ያንፀባርቃሉ።

የሚከተሉትን ማድረግ ከፈለጉ ይህንን ፈተና ይውሰዱ፡

  • ከዲግሪ ደረጃ በታች ሥልጠና ወይም ትምህርት መውሰድ
  • እንግሊዝኛ ቋንቋ በሚነገርበት አገር ውስጥ ከሥራ ጋር ተዛማጅነት ያለው ሥልጠናን መውሰድ
  • እንግሊዝኛ ተናጋሪ ወደ ሆነ አገር መጓዝ
  • በአገርዎ የተሻለ ሥራ ማግኘት ለመቻል።

ወደ ዩኬ ለመጓዝ የሚፈልጉ ከሆነ የዩኬ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ስለሚሰጥ IELTS ፈተና (UKVI) የበለጠ ይወቁ 

የ IELTS Academic ክፍያዎች፡ 183 ፓውንድ (10,400.00 ብር)

ዋጋው ምን ያካተተ ነው? የIELTS ዋጋችን የተመረጡ ጠቃሚ ፈተና መዘጋጃ ስልጠናዎችን፣ ነጻ የመለማመጃ ፈተናዎችንና ሌሎች ግብዓቶችን ያካተተ ነው። 

የጊዜ ርዝመት፡ 2 ሰዓት እና 45 ደቂቃዎች።

ይዘት: ፈተናው አራት ክፍሎች አሉት ፡ ማዳመጥ፣ ማንበብ፣ መጻፍ እና መናገር። የ IELTS ፈተናዎን ለመውሰድ በብሪቲሽ ካውንስል ቦታ ሲይዙ ፈተናው በኦፊሴላዊ የብሪትሽ ካውንስል IELTS ፈተና ማእከል ውስጥ ይከናወናል።

የንግግር ፈተናዎ እንደ ሌሎቹ የፈተና ክፍሎች በተመሳሳይ ቀን፣ ወይም ከሌሎች ፈተናዎች በፊት ወይም በኋላ እስከ አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሊሰጥ ይችላል። የንግግር ፈተናዎ ከዋናው ፈተናዎ በተለየ ቀን ውስጥ የሚሆን ከሆነ አስቀድሞ ማሳወቂያ ይደርስዎታል።

የ ELTS General Training ፈተና ክፍል 1፡ የማዳመጥ ተግባሮች

የጊዜ ርዝመት፡ 30 ደቂቃዎች +10 ደቂቃ ምላሾችዎን ወደ መልስ መስጫው ሉህ ለማስተላለፍ

ቅርጸት፡ 4 የድምፅ ቅጂዎች በተለያየ ዘዬዎች። መልሶችዎን የሚከተሉትን በመጠቀም ይጽፋሉ፡

  • ብዙ ምርጫ
  • ነጥቦችን ማዛመድ
  • የስዕል ማብራሪያ  
  • ዓረፍተ ነገር ማጠናቀቅ

አራት የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎችን ድምጾች ቅጂ ያዳምጡ እና ከዚያም ለበርካታ ጥያቄዎች መልሶችዎን ይጽፋሉ።

  • ቅጂ 1 – በዕለት ተዕለት ማህበራዊ አውድ የተዘጋጀ በሁለት ሰዎች መካከል የሚደረግ ውይይት።
  • ቅጂ 2 - በዕለት ተዕለት ማህበራዊ አውድ የተዘጋጀ የአንድ ሰው ንግግር፣ ለምሳሌ፡ ስለ አካባቢያዊ መገልገያዎች ንግግር።
  • ቅጂ 3 – በትምህርታዊ ወይም የሥልጠና አውድ የተዘጋጀ እስከ አራት በሚደርሱ ሰዎች መካከል የሚደረግ ንግግር፣ ለምሳሌ፡ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እና አንድ ተማሪ ስለ አሳይንመንት ሲወያዩ።
  • ቅጂ 4 - በአንድ የትምርት ዓይነት ላይ የሚደረግ የአንድ ሰው ንግግር፣ ለምሳሌ፡ የዩኒቨርሲቲ ሌክቸር።

ገምጋሚዎች ዋና ዋናዎቹን ሃሳቦች እና ዝርዝር የእውነታ መረጃዎችን፣ የተናጋሪዎች አስተያየቶች እና አመለካከቶችን፣ የአንድ ቃልን ዓላማ እና የሃሳቦችን እድገት የመከታተል ችሎታዎን ለመረዳት ማስረጃዎችን የሚፈልጉ ይሆናል።

የ IELTS General Training ፈተና ክፍል 2፡ የማንበብ ተግባራት

የጊዜ ርዝመት፡ 60 ደቂቃ

ቅርጸት፡

ሶስት የንባብ ምንባቦች ከትግባራት ጋር፡

  • ክፍል 1 - ሁለት አጫጭር ወይም ሦስት አጭር እውነታዊ ጽሁፎች
  • ክፍል 2 - ሁለት አጫጭር ሥራ-ተኮር፣ እውነታዊ ጽሁፎች
  • ክፍል 3 - በአጠቃላይ ርእስ ላይ አንድ ረዘም ያለ ጽሁፍ

የንባብ ክፍሉ በርካታ የማንበብ ክህሎቶችን ለመመዘን የተቀረጹ 40 ጥያቄዎችን ይይዛል። እነዚህም ዋነኞቹን ሀሳቦች ለመረዳት ለማንበብ፣ ለዝርዝር ማንበብ፣ ጭብጥን ማውጣት፣ ምክንያታዊ የሆኑ ክርክሮችን ለመረዳት እና የጸሐፊዎችን አመለካከት፣ ዝንባሌ እና ዓላማ መገንዘብን ያካትታሉ።

ይህም ከመጽሃፍቶች፣ ከመጽሄቶች፣ ጋዜጦች፣ ማሳሰቢያዎች፣ ማስታወቂያዎች፣ የኩባንያ መመሪያ መፅሐፎች እና መመሪያዎችን ያጠቃልላል። እነዚህ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከባቢ ውስጥ በየቀኑ ሊያጋጥሙዎ የሚችሉ ቁሳቁሶች ናቸው።

የ IELTS General Training ፈተና ክፍል 3፡ የመጻፍ ተግባሮች

የጊዜ ርዝመት፡ 60 ደቂቃ

ቅርጸት፡:

  • ደብዳቤ የመጻፍ ተግባር (ቢያንስ 150 ቃላት)
  • አጭር ጽሑፍ የመጻፍ ተግባር (ቢያንስ 250 ቃላት)።

ርዕሰ ጉዳዮች በአጠቃላይ ፍላጎት ዙሪያ ናቸው። ሁለት ተግባራት አሉ፡

  • ተግባር 1 - አንድ ሁኔታ ይቀርብልዎት እና መረጃን የሚጠይቅ ደብዳቤ እንዲጽፉ ወይም ስለሁኔታው ማብራሪያ እንዲሰጡ ይጠየቃሉ። ደብዳቤው ግላዊ፣ ከፊል-መደበኛ ወይም መደበኛ ቅጥ ያለው ሊሆን ይችላል።
  • ተግባር 2 - አንድን አመለካከት፣ ክርክር ወይም ችግር ምላሽ የሚሰጥ ጽሁፍ እንዲጽፉ ይጠየቃሉ። ጽሑፉ በአጻጻፍ ረገድ ግላዊነትን የተላበሰ ሊሆን ይችላል።

የ IELTS General Training ፈተና ክፍል 4፡ የንግግር ተግባራት

የጊዜ ርዝመት፡ ከ 10 - 15 ደቂቃዎች

 ቅርጸት፡

  • የፊት ለፊት ቃለ መጠይቅ።
  • አጠር ያሉ ጥያቄዎች እና በአንድ የተለመደ ርዕሰ ጉዳይ ላይ መናገር።

ልብ ይበሉ፡ እንደ ፈተና ማዕከሉ አካባቢ፣ የፈተናዎን የንግግር ክፍል በተለየ ቀን መያዝ ሊኖርብዎ ይችላል።

Tየንግግሩ ክፍል የንግግር እንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀምዎን ይገመግማል። እያንዳንዱ ፈተና ይቀዳል።

  • ክፍል 1 - ፈታኙ ስለራስዎ እና ስለ ቤት፣ ቤተሰብ፣ ስራ፣ ትምህርት እና ፍላጎቶች ያሉ የተለመዱ ርዕሰ ጉዳዮችን ይጠይቅዎታል። ይህ ክፍል ከአራት እስከ አምስት ደቂቃ ይቆያል።
  • ክፍል 2 - ስለአንድ ርዕስ እንዲናገሩ የሚጠይቅዎ ካርድ ይሰጥዎታል። እስከ ሁለት ደቂቃ ያህል ከመናገርዎ በፊት ለመዘጋጀት አንድ ደቂቃ ይኖርዎታል። ቀጥሎም ፈታኙ በተመሳሳይ ርዕስ ላይ አንድ ወይም ሁለት ጥያቄን ይጠይቃል።
  • ክፍል 3 - በክፍል 2 ውስጥ ስላለው ርዕስ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ይጠየቃሉ። ይህም ተጨማሪ ረቂቅ ሀሳቦችን እና ጉዳዮችን ለመወያየት እድል ይሰጥዎታል። ይህኛው የፈተና ክፍል ከአራት እስከ አምስት ደቂቃ ይቆያል።

ለ IELTS General Training ፈተናዎ ቦታ ይያዙ

ስኬት የሚጀምረው ከ IELTS ነው። ግብዎ ከዲግሪ ደረጃ በታች መማር ወይም እንግሊዝኛ ተናጋሪ ወደ ሆነ አገር መጓዝ ከሆነ፣ እንግዲያውስ የ IELTS General Training ለእርስዎ ትክክለኛ ፈተና ነው።

በብሪትሽ ካውንስል ውስጥ፣ በፈተናዎ ላይ በደንብ እንዲሰሩ የሚያስችሎትን ድጋፍ ለመስጠት ቁርጠኞች ነን። እኛ ጋር ቦታ በሚይዙበት ጊዜ፣ ነፃ ያልተወሰነ የ Road to IELTS Last Minute ኮርስን ያገኛሉ። ይህም ምክር እና የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ዘጠኝ ቪዲዮዎችን፣ 100 መስተጋብራዊ ተግባሮችን እና ለአራቱም ክህሎቶች እያንዳንዳቸው ሁለት የ IELTS General Training ፈተናዎችን ያጠቃልላል።

የ IELTS General Training ፈተና ቀንን ያግኙ። 

ለፈተናዎ ቦታ ከመያዝዎ በፊት ለሚያመለክቱባቸው ድርጅቶች የትኛውን ፈተና እንደሚፈልጉ መፈተሽዎን ያረጋግጡ።