IELTS books
IELTS books

ለIELTS ፈተና ለመዘጋጀት ሊረዱዎት የሚችሉ በተለይ ሁለት መጽሐፎችን ልንጠቁምዎት እንወዳለን።

How to prepare for IELTS

How to prepare for IELTS፣ብሪቲሽ ካውንስል ያዘጋጀው ጽሑፍ ሲሆን ፈተናው ላካተታቸው አራት ክፍሎች ይኸውም ለመስማት፣ ለማንበብ፣ ለመጻፍ እና ለመናገር ፈተናዎች የሚጠቅሙ ምክሮችን፣መልመጃዎችንና ተግባራዊ ፈተናዎችን ይዟል። ጽሑፉ ስለ IELTS የትምህርት ተቋምና ስለ IELTS አጠቃላይ ፈተና ይገልፃል።

ከማዳመጥና ከመናገር ጋር የተያያዙ ተጨምቀው የተወሰዱ ቃለ ምልልሶችን የያዘ ሲዲ ከመጽሐፉ ጋር ይገኛል። መጽሐፉ ቤት ውስጥ ለማጥናትም ሆነ ለክፍል ትምህርት ጠቃሚ ነው።

መጽሐፉን ማግኘት ከፈለጉ እባክዎ ወደ ብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ ይምጡና የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን ያነጋግሩ።

IELTS Official Practice Materials Volume 2

IELTS Official Practice Materials Volume 2፣ Academic እና General Training ስልጠና ስር ላሉት ለሁሉም የትምህርት ዓይነቶች የናሙና ፈተናዎችን አካትቷል። እነርሱም፦ መስማት፣ ማንበብ፣ መጻፍ እና መናገር፤ እንዲሁም ፈተና አዘጋጆች የሰጧቸውን ሐሳቦች ከመልሶቹ ጋር ያቀርባል።

በተጨማሪም መጽሐፉ ለልምምድ የቀረበ የመስማት ፈተና፣ የናሙና ፈተናዎቹ መልሶች እንዲሁም ሦስት ተማሪዎች የንግግር ፈተናውን ሲፈተኑ የሚያሳዩ ሦስት የቪዲዮ ክሊፖችን የያዘ ዲቪዲ አለው።

መጽሐፉን ማግኘት ከፈለጉ እባክዎ ወደ ብሪቲሽ ካውንስል ቢሮ ይምጡና የደንበኞች አገልግሎት ቡድኑን ያነጋግሩ።