Road to IELTS፣ ለፈተና ለመዘጋጀት የሚረዳ በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የብሪቲሽ ካውንስል ስመ ጥር ኮርስ ነው። ይህ ኮርስ ለ IELTS ፈተና በጥሩ ሁኔታ እንዲዘጋጁ ይረዳዎታል። Road to IELTS ሲጠቀሙ ከዚህ በታች የተገለፁትን ነገሮች ያገኛሉ፦ 

  • ለ Academic አና General Training የ IELTS ፈተናዎች የሚጠቅሙ በኢንተርኔት ላይ የሚገኙ መማሪያዎች
  • ለመስማት፣ ለማንበብ፣ ለመጻፍ እና ለንግግር ፈተናዎች የሚያዘጋጁዎት በኢንተርኔት ላይ በሚገኙ በመጻሕፍት የሚደገፉ መለማመጃዎች
  • ቀደም ባሉት ጊዜያት ከነበሩ ተፈታኞች የተገኙ በናሙና ቪዲዮዎች የሚቀርቡ መረጃዎች
  • በሚፈተኑበት ወቅት ምን መደረግ እንዳለበትና እንደሌለበት የሚያጎላ የመምህራን ማስተማሪያ
  • የሰአት ገደብ ያላቸው መልመጃ ፈተናዎች
  • የራስዎን ብቃት በዓለም ዙሪያ ካሉ ሌሎች ተማሪዎች ብቃት ጋር ማወዳደር የሚችሉበት “ማይፕሮግረስ” የሚል ርእስ ያለው ክፍል
  • የፈተና ቀንዎትን የሚያስታውስዎት “ማይፕሮፋይል” የሚል ክፍል 

Road to IELTS በምን ረገድ ይረዳኛል?

Road to IELTS በአንዳንድ አስፈላጊ መንገዶች ይረዳዎታል፦

  • የራስዎን መሻሻል መገምገም የሚያስችል ብቃትዎን የሚመለከት አስተያየት ወዲያውኑ ይሰጥዎታል
  • ምን እንደተሳሳቱ ማወቅ እንዲችሉ የመልመጃ ጥያቄዎችን ትክክለኛ መልስ ያገኛሉ
  • የፈተና አሰራርዎን እንዲያሻሽሉ የሚረዱ ሃሳቦችና መረጃዎች ያገኛሉ
  • ፈተናውን ከመውሰድዎ በፊት በራስ የመተማመን ስሜትዎን እንዲያዳብሩ የሚያስችሉዎት በእውነተኛው የ IELTS ፈተና ላይ የተመሰረቱ መልመጃዎች ይሰራሉ

Road to IELTS መማሪያዎቻችንን አሁኑኑ ለ10 ሰአታት ያህል በነፃ መሞከር ይችላሉ።

IELTS ፈተና ለመፈተን እኛ ዘንድ ከተመዘገቡ መማሪያዎቹን ለተጨማሪ 20 ሰአታት በነፃ መጠቀም ይችላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ በኢንተርኔት ላይ የሚገኘውን ሙሉውን መማሪያ በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት እና ስለ ክፍያው መረጃ ለማግኘት Road to IELTS የሚለውን ሊንክ መመልከት ይችላሉ።

ምን አይነት Road to IELTS መማሪያዎች አሉ?  የትኛውን መማሪያ ማግኘት እችላለሁ?  
Road To IELTS : Test Drive ማንኛውም ሰው በነፃ ሊያገኘው የሚችል 10 ሰአታት የሚፈጅ መማሪያ  
Road To IELTS : Last Minute IELTS ለመፈተን ብሪቲሽ ካውንስል የተመዘገቡ ተፈታኞች በሙሉ በነፃ ሊያገኙት የሚችሉ 20 ሰአታት የሚፈጅ (በአጠቃላይ 30 ይሆናል) መማሪያ  
Road To IELTS : Full Version ማንኛውም ሰው ሊገዛው የሚችል 120 ሰአታት የሚፈጅ መማሪያ