IELTS በመፈተን አውስትራሊያ ለመማር፣ እዚያ ለመሥራት ወይም ለመጓዝ የሚያስችል ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታ እንዳለዎት ያሳዩ። በአውስትራሊያ የሚገኙ ወደ 900 የሚጠጉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ፕሮግራሞች የIELTS ፈተና ውጤት የላቀ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ማረጋገጫ እንሆነ ይቀበላሉ።
በአውስትራሊያ መማር ወይም መሥራት
በአውስትራሊያ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ድርጅቶች እንግሊዝኛ በመረዳት፣ በማንበብ፣ በመጻፍና በመናገር ረገድ ያለዎትን ችሎታ IELTS በትክክል ማየት እንደሚቻል ያውቃሉ። ፈተናውን ያዘጋጁት የእንግሊዝኛ ቋንቋን በመገምገም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንቱ ከተባሉ ባለሙያዎች መካከል ይገኙበታል።
ድርጅታችን ያዘጋጀው የኢንተርኔት ማሰሻ ፕሮግራም IELTSን የሚቀበሉትን በአውስትራሊያ የሚገኙ የሁሉንም ድርጅቶች ዝርዝር መረጃ ይዟል። በአውስትራሊያ ስለ መማርStudy in Australiaእንደተባሉ ካሉ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ወደ አውስትራሊያ መጓዝ
በአውስትራሊያ የጉዞ ቪዛ ደንብ መሠረት IELTS ፈተና ወደ አገሪቱ ለመግባት ከሚደረገው የጉዞ ዝግጅት ሂደት አንዱ ወሳኝ ክፍል ነው።
ዋናዎቹ የቪዛ አመልካቾች፣ የትዳር ጓደኞቻቸው እንዲሁም በእነርሱ ስር ያሉ ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው አዋቂዎች ይህን ፈተና እንዲወስዱ ይጠበቅባቸዋል። IELTS ለመፈተን ከመመዝገብዎ በፊት በአውስትራሊያ ተቀባይነት ለማግኘት ምን ያህል የIELTS ውጤት ማምጣት እንዳለብዎት እንዲሁም የትኛውን ፈተና (የቀለም ትምህርት ወይም አጠቃላይ ስልጠና) መውሰድ እንዳለብዎት ማወቅ ይኖርብዎታል።
ወደ አውስትራሊያ ስለ መግባትና የተማሪ ቪዛ ለማግኘት እንዴት ማመልከት እንዳለብዎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት Australian Government Department of Immigration and Citizenship የሚለውን ድረገጽ ይመልከቱ።