©

British Council

IELTS ፈተና በመፈተን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለመማር የሚያስችል ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታ እንዳለዎት ያስመስክሩ። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ፕሮግራሞች የIELTS ፈተና ውጤት የላቀ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ማረጋገጫ እንደሆነ ይቀበላሉ።

በመላው ዩናትድ ስቴትስ የሚገኙ ግዙፍ ተቋማት፣ እንግሊዝኛ በመረዳት፣ በማንበብ፣ በመጻፍና በመናገር ረገድ ያለዎትን ችሎታ IELTS በትክክል እንደሚያሳይ ያውቃሉ። IELTS ፈተና

  • ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኙ 25 ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ዘንድ ተአማኒነት አለው
  • በሁሉም የአይቪ ሊግ ኮሌጆች ዘንድ ተቀባይነት አለው
  • በዩናትድ ስቴትስ የሚገኙ50 ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ለማስተማር በፕሮግራማቸው አካትተውታል

የIELTS ውጤትዎ ጥሩ ከሆነ በመረጡት ዩኒቨርስቲ የመማር አጋጣሚ ያገኛሉ።ማግኘት ያለብዎት የIELTS ውጤት የሚለውን ሊንክ ይመልከቱ።

በዩናትድ ስቴትስ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ስለ IELTS ምን ይላሉ?

“IELTS በጣም ጥሩ ፈተና እንደሆነ አምናለሁ፤ ምክንያቱም ካንሳስ ስቴት ዩኒቨርስቲ ይጠቀምበታል!”

- ካንሳስ ስቴት ዩኒቨርስቲ፣ ሚራንዳ አሴቤዶ

“የIELTS ፈተናን ለTOEFL እንደ አማራጭ አድርገን ለመቀበል ከመወሰናችን በፊት እኔ ራሴ ፈተናውን ተፈትኛለሁ፤ ፈተናው በጣም ጠንከር እንደሚልም አረጋግጫለሁ።”

- ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ፣ ኒው ዮርክ ጄምስ ኤፍ ሚንተር

“ከ2002 ጀምሮ IELTS በእኛ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል፤ የአንድን ሰው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ለመመዘን የሚያስችል አግባብነት ያለው ፈተና እንደሆነ እናምናለን። በተለይ የንግግር ችሎታን ለመመዘን የተዘጋጀው ክፍል በጣም ጥሩ ነው።”

- ሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ፣ ዲንትሳንቲር

“IELTS በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኝ መሆኑ ይበልጥ ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል። በዓለም ዙሪያ ያሉ አመልካቾች የሚሰጡት ምላሽ አስደሳች ነው።”

- ዩሲኤልኤ የምሩቃን ቅበላ ዳይሬክተር፣ ዳንየል ጄ ቤኔት

ውጫዊ ማያዣዣዎች