Woman puts pins on a map of the world

በመረጡት አገር ለመማር ሲያመለክቱ አስቀድሞ የታሰበበት እቅድ ማውጣት ያስፈልግዎታል። የደረሱበትን ደረጃ ለመከታተል፣ ባዘጋጀነው የመቆጣጠሪያ ቅጽ ይጠቀሙ።

ከምዝገባ በፊት ባለው የ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ

ሊማሩበት የሚፈልጉትን ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርስቲ ይምረጡ፤ የትኛው የIELTS ክፍልና ምን ያህል ውጤት ማግኘት እንደሚያስፈልግዎት ያጣሩ። እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ለማወቅ IELTS ለመፈተን መመዝገብ የሚለውን ሊንክ ይመልከቱ።

●      አሁን በሚማሩበት ተቋም ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ይጣሩ።

●      በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የIELTS ፈተና ማእከል ይወቁ፣ የሚያመችዎትን ቀን ይምረጡ እንዲሁም የሚፈተኑትን ፈተና ያስመዝግቡ። ስልጠና ለመውሰድ ከመመዝገብዎ ከ12 – 14 ወራት ቀደም ብለው ፈተናውን ለመፈተን እቅድ ማውጣት ይኖርብዎታል። ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት IELTS ለመፈተን መመዝገብ የሚለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

●      አፍ መፍቻ ቋንቋዎ እንግሊዝኛ ቢሆንም እንኳ IELTS ለመፈተን ዝግጅት ማድረግ ይጀምሩ። ከፈተናው አቀራረብና ከጊዜ ገደቡ ጋር መተዋወቅ ይኖርብዎታል።

●      ሊማሩባቸው የሚፈልጓቸው ተቋማት የመግቢያ ፈተና እንዳላቸው ያጣሩ። የመረጧቸው ተቋማት የሚፈልጓቸውን ፈተና/ፈተናዎች ለመውሰድ ከወዲሁ እቅድ ያውጡ።

ከምዝገባ በፊት ባሉት ከ15-18 ወራት

የትምህርት እድልን በተመለከተ እንደሚከተሉት ያሉ ድርጅቶች የሚያወጡትን መረጃ ይመልከቱ፦

●      ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር በተያያዘEducation UKእናUCAS

●      ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በተያያዘEducation USA

●      ከአውስትራሊያ ጋር በተያያዘStudy in Australia

ከምዝገባ በፊት ባሉት ከ12-14 ወራት

●      IELTS ፈተና ይፈተኑና በ13 ቀናት ውስጥ ውጤትዎን ይቀበሉ። ተፈላጊውን ውጤት ባያገኙ ውጤትዎን እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ የሚረዱ ሃሳቦች ለማግኘትየትምህርት ዓይነቶችና ማስተማሪያዎችየሚለውን ሊንክ ይመልከቱ።

●      ማመልከት ለሚፈልጉበት ለእያንዳንዱ ተቋም ፋይል ያዘጋጁና ሁሉንም ቅጾች፣ የተፃፃፏቸውን ደብዳቤዎችና ደረሰኞች በአግባቡ ያስቀምጡ።

●      ማመልከቻዎችን በሙሉ በጥንቃቄ ያንብቡ፤ የሚጠበቁቡዎትን ነገሮች ጊዜው ከማለፉ በፊት ያሟሉ። ጉዳዮችዎን በአግባቡ ለመፈጸም ያከናወኗቸውን ነገሮች የሚመዘግቡበት የቀን መቁጠሪያ ያዘጋጁ።

ከምዝገባ በፊት ባሉት ከ10-12 ወራት

●      የመረጡት ተቋም (ተቋሞች) ያዘጋጀውን የመግቢያ ማመልከቻ ይሙሉ።

●      የገንዘብ ድጋፍና ነፃ የትምህርት እድል ለማግኘት ማመልከቻ ይሙሉ።

●      ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸውን ነገሮች ያጣሩ።

ከምዝገባ በፊት ባሉት ከ6-9 ወራት

በዚህ ጊዜ የትኞቹ ተቋማት በተማሪነት እንደተቀበሉዎት አውቀው መሆን ይኖርበታል።

ከምዝገባ በፊት ባሉት 3 ወራት

ቪዛ ለማግኘት ያቀረቡት ማመልከቻ እንዳይጓተት ክትትል ያድርጉ።

ውጫዊ ማያዣዣዎች